መስከረም 27/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከመስከረም 10/2017ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት ከመላ ሀገሪቱ ገጠርና ከተማ በተመረጡ 2,881 የቆጠራ ቦታዎች ሲካሄድ የነበረው ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት የመስክ ስራ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለፀ። የመስክ ስራ መጠናቀቁን በማስመልከት በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በተሰጠው መግለጫ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የጥናቱ የመስክ ስራ በታቀደው መሰረት እንዲጠናቀቅ […]