ሰኔ 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስርዓተ ፆታና የአካል ጉዳተኞች ስታቲስቲክስ መረጃዎችን በጥናት፣ በቆጠራና በአስተዳደራዊ መዛግብት መረጃዎች ለማካተት የሚያስችል መመሪያ ላይ ከተቋሙ መሪ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት አደረገ። በውይይት መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስነ-ሕዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይናለም ተሻገር የስርዓተ ፆታና የአካል ጉዳተኞች ስታቲስቲክስ የመረጃ ክፍተት መኖሩን ገልፀው ፤ ተቋሙ በሚያዘጋጃቸው የጥናትና ቆጠራ መረጃዎች ወጥና አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የስርዓተ ፆታና የአካል ጉዳተኞች ስታቲስቲክስ መረጃዎች እንዲካተቱ ለማስቻል መመሪያው መዘጋጀቱን አንስተው ሁሉም ጥናትና ቆጠራ የሚያከናውኑ የስራ ክፍሎች ለመመሪያው ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች እንዲሰጡ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል። የስርዓተ ፆታ፣ የአካል ጉዳተኝነት ስታቲስቲክስ መረጃዎችን ከጥናትና ቆጠራ