ግንቦት 21/2017ዓ.ም አዳማ፣ የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የግብርና ቆጠራ አስመልክቶ የተቋሙ አመራሮች፣ ባለሞያዎች እና የአለም አቀፉ የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ተወካዮች በአዳማና ቢሾፍቱ ዙሪያ የመስክ ጉብኝት አካሄዱ። በመስክ ጉብኝቱ የንግድ እርሻዎች ፣ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው የቤተሰብ እርሻ እና የእንስሳት እርባታዎች ላይ ምልከታ የተደረገ ሲሆን የግብርና ቆጠራ ስራው በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ከመስክ ምልከታው ለመረዳት ተችሏል።
ግንቦት 19/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017ዓ.ም እያካሄደ በሚገኘው የግብርና ቆጠራ አፈፃፀምና በቀጣይ ቀሪ የቆጠራው ተግባራት ላይ ከአለም አቀፍ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ጋር ውይይት አደረገ። የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋሙ ለሁለተኛ ጊዜ እያካሄደ የሚገኘውን የግብርና ቆጠራ ከፍተኛ በሆነ በመንግስትና አጋር ድርጅቶች ድጋፍ አሁን ያለበት ውጤታማ የሆነ አፈፃፀም ላይ መድረሱን ገልፀው አለም አቀፍ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) እያደረገ ላለው የቴክኒክ ድጋፍ በተቋሙ ስም አመስግነዋል። ተቋሙ በቀጣይ ቀሪ የቆጠራው ተግባራት ከድርጅቱ የቴክኖሎጂና የቴክኒክ ድጋፍ እንደሚፈልግም ዋና ዳይሬክተሩ አክለው ገልፀዋል። የአለም አቀፍ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) የግብርና ቆጠራ ቡድን መሪ ሄሮ ካስታኖ (Ph.D) የግብርና ቆጠራው ጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሆነ እና በቀጣይ ቀሪ ስራዎች ላይ ከተቋሙ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል። የግብርና ቆጠራ ከቅድመ ዝግጅት አሁን እስካለበት ደረጃ ያለውን አፈፃፀም እንዲሁም ቀሪ ተግባራትን የሚያሳይ ገለፃ በግብርና ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱላዚዝ ሽፋ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች በኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬና በተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያዎች ምላሽ ተሰቶበታል።
ግንቦት 11/2017ዓ.ም፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትና ኖርዌይ ስታቲስቲክስ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በበይነ መረብ (Virtual meeting) ውይይት አደረጉ። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2024/25ከኖርዌይ ስታቲስቲክስ ጋር በነበሩት ፕሮጀክቶች በርካታ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የልምድ ልውውጦች መገኘታቸው ተገልጿል። በቀጣይ በሚኖረው ፕሮጀክትም በቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ፣ በጥናት ስነ-ዘዴ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት መሆናቸው በውይይቱ ተነስቷል።
ግንቦት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራር በ2017በጀት ዓመት በአስተዳደር ዘርፍ በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ከሚመለከታቸው ስራ አስፈፃሚዎች ጋር የስራ ግምገማ አደረገ። በግምገማ መድረኩ በ2017በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት በአስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ሁሴን አጎናፍር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገልፀው በቀሩት ቀጣይ ጊዜያት መሻሻል ያለባቸው ተግባራት ላይ አቅጣጫ በመስጠት የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል።
ግንቦት 5/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች በ2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ዋና ዋና እቅዶችና በጀት ዝግጅት ላይ ውይይት አደረጉ።
ግንቦት 5/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የ2024 ኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ ጤና ጥናት ከመስክ መረጃ የመሰብሰብ ተግባር ማጠናቀቁን ለሀገር አቀፍ አብይ ኮሚቴና አለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ገለፀ። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር…
ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፌደራል ሥነ-ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር “ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ’’ በሚል መሪ ቃል ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ…
ሚያዚያ 29/2017ዓ.ም አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሁለተኛ ዙር የግብርና ቆጠራ የዘጠኝ ወራት የመስክ ስራ አፈፃፀም ለተቋሙ የግብርና ቆጠራ አስተባባሪ ኮሚቴ ቀርቦ ውይይት ተደረገ። ለውይይቱ መነሻ የሚሆነውን የዘጠኝ ወራት የስራ…
ሚያዚያ 22/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የስታቲስቲክስ ኖርዌይ ከምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) ጋር በመተባበር የምግብ ዋስትና ስታቲስቲክስ (Food security Statistics) መረጃ ለመተንተን የሚያስችል ስልጠና ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የቤተሰብ በጀትና ሌበር…
ሚያዚያ 22/2017 ዓ.ም፣አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስርዓተ ፆታ ስታቲስቲክስ መረጃ አሰባሰብና ጥራቱን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ ከአጋር የልማት ድርጅቶች ጋር ውይይት አደረገ። ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የማህበራዊና አካቶ…