ጥር 18/2018 ዓ.ም ቢሾፍቱ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የሚውሉ ካርታዎች ወቅታዊ ለማድረግ የሚያግዝ ስልጠና ከዋና መስሪያ ቤት፣ ከአዲስ አበባ፣ ከአዳማና ከአምቦ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተውጣጡ ባለሙያዎች እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የተቋሙ የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው የቆጠራ ካርታ ስራ ለቆጠራዎችና ለጥናቶች መረጃ ለመሰብሰብ ዋነኛና ወሳኝ ግብዓት መሆኑን አንስተው ሰልጣኞች ካርታውን ለመስራት የሚያስችል ዕውቀትና ክህሎት በማግኘት ትክክለኛና ጥራት ያለው ስራ ለመስራት ስልጠናውን በትኩረት እንድትከታተሉ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ስልጠናው በካርታ ዝግጅት ባተኮሩ ርዕሶች ላይ የጽንሰ ሀሳብና የተግባር ስልጠና ከጥር 18 እስከ የካቲት 1/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
