ሚያዚያ 5/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለሚያካሂደው የመንግስት ሰራተኞችን ፐርሶኔል መረጃ ለማረጋገጥ በመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ስልጠና ለሚሰማሩ ከዋናው መ/ቤትና ከሲቪል ሰርቪስ ለተውጣጡ የቴክኒክና የሎጂስቲክ አስተባባሪዎች ኦረንቴሽንና የስራ ስምሪት ተሰጠ።


በመድረኩ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋሙ ከዚህ ቀደም ትላልቅ ሀገራዊ ቆጠራዎችና ጥናቶችን በስኬት ማከናወኑን አንስተው ይህን ሀገራዊ ስራም ከዚህ ቀደም የነበሩትን ልምዶች በመጠቀም ወጥና ፈጠራ በታከለበት መንገድ በቅንጅት በመስራት ለማሳካት እንሰራለን ያሉ ሲሆን ለዚህ ስልጠና በአስተባባሪነት የተመደባችሁ ባለሙያዎች ስልጠናው በተሳካ መንገድ እንዲከናወን ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ሲሉ የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በኦረንቴሽኑ ላይ በስልጠናው ላይ ከዋናው መ/ቤት ወደየማዕከላቱ የሚሄዱ አስተባባሪዎች ማድረግ ስለሚጠበቅባቸውና ከሰልጣኞችም ስለሚጠበቁ ተግባራት ገለፃ የቀረበ ሲሆን ከባለሙያዎቹ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል።




