ተቋማቱ በጋራ ለመስራት የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረሙ

       ግንቦት 14/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በሀገራችን በምርምርና ልማት ዘርፍ ያለውን የመረጃ ክፍተት የሚሞላ ብሔራዊ የምርምርና ልማት ጥናት በጋራ ለማካሄድ  የሚያስችል የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ።

t8a3400

ስምምነቱን የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ እና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ በጋራ ፈርመውታል።

t8a3382

የጥናቱ  ዋና ዓላማ የምርምርና ልማት ወጪን ከሀገር ውስጥ ጠቅላላ ምርት አንፃር ለመለካት፣ በዘርፉ የተሰማሩ ባለሙያዎችን ብዛት ለማወቅ፣ የምርምር ዓይነቶችን ለመለየት፣ የአሠራር ፈተናዎችንና ክፍተቶችን በማጥናት መነሻ አመልካች መረጃ ለማዘጋጀትና ከጥናቱ ከተገኙት መረጃዎች በመነሳት ተግባራዊ የሚሆኑ የፖሊሲ ምክረ-ሀሳቦችን ማቅረብ ሲሆን መረጃው ከንግድ ድርጅቶች፣  ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ ከመንግሥት መሥሪያ ቤቶችና ለትርፍ ያልተቋቋሙ የግል ድርጅቶች እንደሚሰበሰብ በፊርማ ስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

t8a3359

ጥናቱ ለ2030 የዘላቂ ልማት ግቦች (ለኢንዱስትሪ፣ ፈጠራና መሠረተ ልማት)፣ ለአፍሪካ አጀንዳ 2063  የሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ስትራቴጂ)፣ ለሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያ እና ለኢትዮጵያ የ10 ዓመት መሪ የልማት ዕቅድ ስኬት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተገልጿል።

t8a3385