የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች መረጃ የማረጋገጥ የመጀመሪያ ዙር የመስክ ስራ አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ

ግንቦት 28/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር እያካሄደ በሚገኘው የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች መረጃ የማረጋገጥ ስራ የመጀመሪያ የመስክ ስራ አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ።

t8a3720


በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስነ ህዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ አይናለም ተሻገር የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጥ የመስክ ስራ ለመደገፍ ከዋናው መስሪያ ቤት ወደቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የሄዳችሁ ባለሙያዎች ስራውን እንዴት እየተካሄደ እንደሆነ፣ በመስክ ስራው የተገኙ ዋና ዋና ግኝቶች፣ መልካም ተሞክሮዎች፣ ያጋጠሙ ችግሮች፣ የተወሰዱ መፍትሔዎችና በቀጣይ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች ላይ በመወያየት ከዚህ የአፈፃፀም ግምገማ የምናገኛቸውን መረጃዎች እንደግብዓት በመውሰድ ጥራትና ወቅታዊነቱን የጠበቀ መረጃ ለማቅረብ መስራት አለብን ሲሉ ገልፀዋል።
በመድረኩ በመስክ በነበሩ ባለሙያዎች የስራው አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

t8a3783


የመድረኩን ማጠቃለያ ያደረጉት የስነ ህዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይናለም ተሻገር በሪፖርቱ ለቀረቡት ችግሮች የመፍትሄ ሀሳቦችን ጠቁመው፤ ካለፈው ስራ ልምድ በመውሰድና የታዩ ክፍተቶችን በማስተካከል በቀጣይ ከዚህ በተሻለ ትኩረት ሰጥተን መስራት ይጠበቅብናል ሲሉ ተናግረዋል።

t8a3758
t8a3724
t8a3736
t8a3732