መጋቢት 29/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣


የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች በተቋሙ ዋና መ/ቤት በተከናወኑ የህንፃ ጥገና፣ ግንባታና ሪኢኖቬሽን ስራዎች ለኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ስራዎች ኮርፖሬሽን እውቅና የመስጠት መርሃ ግብር አካሄደ።
በመርሀ ግብሩ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋሙ ከ2016 ዓ.ም ጀምሮ የሪፎርም ተግባራትን እያከናወነ መሆኑን አንስተው በሪፎርም ተግባሩ የትኩረት አቅጣጫ ከሆኑት እቅዶች ምቹ የስራ ከባቢን መፍጠር አንዱና ዋነኛው መሆኑን ገልፀው፣ ድርጅቱ በተቋሙ ባከናወናቸው የጥገናና የሪኢኖቬሽን ስራ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ስራው በኃላፊነትና በጥራት የተገነባና ከትውልድ ትውልድ ሊተላለፍ የሚችል መሆኑን ገልፀው በስራው ለተሳተፉ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በመጨረሻም በተቋሙ የተሰሩትን የሪኢኖቬሽን ስራዎች ጉብኝት ተደርጎ በስራው ለተሳተፉ አካላት የዕውቅናና የምስጋና የምስክር ወረቀት ተሰጥቷል።








