ለተቋሙ ሴቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

aa3a1487

ግንቦት 25/2017ዓ.ም አዳማ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሴቶችን ለማብቃት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትና ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ሰጠ። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብነት ሀዋዝ እንደተቋም ሴቶችን ማብቃትና ወደ አመራር  ማምጣት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራበት መሆኑን አንስተው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በሰራው ሪፎርም ሴቶችን ወደ አመራር በማምጣት ሌሎች ባለሙያዎችንም ለማብቃት እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል።  ስልጠናውን በስርዓተ ፆታ፣ የማካተት ፅንሰ ሀሳብ አስፈላጊነት፣ ስልቶች፣ ተግዳሮቶችና ልዩ ትኩረት የሚፈልጉ የማህበረሰብ ክፍሎች  ፍላጎቶች ላይ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመጡት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጌታቸው ካሴ እየተሰጠ ይገኛል። ስልጠናው ከተለያዩ የስራ ክፍል ለተውጣጡ 45 ባለሙያዎች ለቀጣይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀግብር ለመረዳት ተችሏል።

የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት የስራ ጉብኝት አደረገ

aa3a9861

ግንቦት 21/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከ2015−2017ዓ.ም በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የተከናወኑ ዋና ዋና የሪፎርም ለውጥ ስራዎች  በተመለከተ የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ በክቡር አቶ ደሳለኝ ወዳጆ የተመራ ቡድን የስራ ጉብኝት አደረገ። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር  ዶ/ር በከር ሻሌ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈው ተቋሙ በቋሚ ኮሚቴው ከዚህ በፊት ሲጎበኝ  የሰጣቸውን  አስተያየቶች  እንደግብዓት በመውሰድ የሰራቸውን የለውጥ ስራዎች ለማሳየት የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል። ተቋሙ ከ2015−2017ዓ.ም በሪፎርም ያከናወናቸው ዋና ዋና ለውጦች የተቋሙ መዋቅራዊ አደረጃጀት፣ የሰው ሀይል አቅም ግንባታ፣  ምቹ የስራ ከባቢ መፍጠር፣ የጥናት ስነ−ዘዴዎችን ማሻሻልና ሌሎች ሰፊ የመረጃ ልማት ስራዎች የደረሱበት ደረጃ በተመለከተ  በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ሁሴን አጎናፍር ሪፖርት ቀርቧል። የፕላን፣ በጀት እና ፋይናንስ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ አቶ ደሳለኝ ወዳጆ እና አባላት ተቋሙን ከዚህ ቀደም ሲጎበኙ በጣም  ብዙ ክፍተቶች የነበረበት መሆኑን አንስተው ዛሬ በመስክ ምልከታው ወቅት የታዩትን መሻሻሎች በማድነቅ ይህ በጎ ለውጥ ተጠናክሮ  እንዲቀጥል እና ለመረጃ ጥራት ከፍተኛ ድርሻ ያላቸውን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶችንም በዚሁ መልኩ የተሻሉ እንዲሆኑ ለማድረግ  ትኩረት  እንዲሰጥ አስገንዝቧል::

የስርዓተ ፆታና የአካል ጉዳተኞች ስታቲስቲክስ መመሪያ ዝግጅት ላይ ውይይት ተደረገ

photo 1 2025 07 18 11 22 19

ሰኔ 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስርዓተ ፆታና የአካል ጉዳተኞች ስታቲስቲክስ መረጃዎችን በጥናት፣ በቆጠራና በአስተዳደራዊ መዛግብት መረጃዎች ለማካተት የሚያስችል መመሪያ ላይ ከተቋሙ መሪ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት አደረገ። በውይይት መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስነ-ሕዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይናለም ተሻገር የስርዓተ ፆታና የአካል ጉዳተኞች ስታቲስቲክስ የመረጃ ክፍተት መኖሩን ገልፀው፤ ተቋሙ […]

የግብርና ቆጠራ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ

1t8a0410

ግንቦት 21/2017ዓ.ም አዳማ፣ የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የግብርና ቆጠራ አስመልክቶ የተቋሙ አመራሮች፣ ባለሞያዎች እና የአለም አቀፉ የምግብና እርሻ  ድርጅት (FAO) ተወካዮች በአዳማና ቢሾፍቱ ዙሪያ የመስክ ጉብኝት አካሄዱ። በመስክ ጉብኝቱ የንግድ እርሻዎች ፣ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው የቤተሰብ እርሻ እና የእንስሳት እርባታዎች ላይ ምልከታ የተደረገ ሲሆን የግብርና ቆጠራ ስራው በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ከመስክ ምልከታው ለመረዳት ተችሏል።

በግብርና ቆጠራ አፈፃፀም ከአለም አቀፍ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ጋር ውይይት ተደረገ

aa3a9589

ግንቦት 19/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017ዓ.ም እያካሄደ በሚገኘው የግብርና ቆጠራ አፈፃፀምና በቀጣይ ቀሪ የቆጠራው ተግባራት ላይ  ከአለም አቀፍ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ጋር ውይይት አደረገ። የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋሙ ለሁለተኛ ጊዜ እያካሄደ የሚገኘውን የግብርና ቆጠራ ከፍተኛ በሆነ በመንግስትና አጋር ድርጅቶች ድጋፍ አሁን  ያለበት ውጤታማ የሆነ አፈፃፀም ላይ መድረሱን ገልፀው አለም አቀፍ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) እያደረገ ላለው የቴክኒክ ድጋፍ በተቋሙ ስም አመስግነዋል። ተቋሙ በቀጣይ ቀሪ የቆጠራው ተግባራት ከድርጅቱ የቴክኖሎጂና  የቴክኒክ  ድጋፍ እንደሚፈልግም ዋና ዳይሬክተሩ አክለው ገልፀዋል።  የአለም አቀፍ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) የግብርና ቆጠራ ቡድን መሪ ሄሮ ካስታኖ (Ph.D) የግብርና ቆጠራው ጥሩ አፈፃፀም ላይ እንደሆነ እና በቀጣይ ቀሪ ስራዎች ላይ ከተቋሙ ጋር በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀዋል።  የግብርና ቆጠራ ከቅድመ ዝግጅት አሁን እስካለበት ደረጃ ያለውን አፈፃፀም እንዲሁም ቀሪ ተግባራትን የሚያሳይ ገለፃ በግብርና  ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱላዚዝ ሽፋ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችና አስተያየቶች  በኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬና በተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያዎች ምላሽ ተሰቶበታል።

ተቋማቱ በቀጣይ በትብብር ለመስራት የሚያስችል ውይይት አደረጉ

ssb3

ግንቦት 11/2017ዓ.ም፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትና ኖርዌይ ስታቲስቲክስ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በበይነ መረብ (Virtual meeting) ውይይት አደረጉ።  የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2024/25ከኖርዌይ ስታቲስቲክስ ጋር በነበሩት ፕሮጀክቶች በርካታ የአቅም ግንባታ  ስልጠናዎች  የልምድ ልውውጦች መገኘታቸው ተገልጿል።  በቀጣይ በሚኖረው ፕሮጀክትም በቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ፣ በጥናት ስነ-ዘዴ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ትኩረት  የሚሰጣቸው ተግባራት መሆናቸው በውይይቱ ተነስቷል።

በአስተዳደር ዘርፍ የዘጠኝ ወራት ስራ አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ

006

ግንቦት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራር በ2017በጀት ዓመት በአስተዳደር ዘርፍ በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ከሚመለከታቸው ስራ አስፈፃሚዎች ጋር የስራ ግምገማ አደረገ። በግምገማ መድረኩ በ2017በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት በአስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ሁሴን አጎናፍር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በመጨረሻም የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገልፀው በቀሩት ቀጣይ ጊዜያት መሻሻል ያለባቸው ተግባራት ላይ አቅጣጫ በመስጠት የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል።

የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብና ጤና ጥናት ከመስክ መረጃ የመሰብሰብ ተግባር ተጠናቀቀ

aa3a9519

ግንቦት 5/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የ2024 ኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ ጤና ጥናት ከመስክ መረጃ የመሰብሰብ ተግባር ማጠናቀቁን ለሀገር አቀፍ አብይ ኮሚቴና አለም አቀፍ አጋር ድርጅቶች ገለፀ። የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ መድረኩ የተዘጋጀው አምስተኛ ዙር የኢትዮጵያ ሥነ-ህዝብ ጤና ጥናት ከመስክ መረጃ የመሰብሰብ ተግባር መጠናቀቁንና ጥናቱ አሁን ላይ የደረሰበትን ደረጃ ለማሳወቅ የተዘጋጀ መሆኑን […]

ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

1t8a8130

ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፌደራል ሥነ-ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር “ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ’’ በሚል መሪ ቃል ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች እየሰጠ ይገኛል። ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ሙስና ለሀገራችን ልማትና ዕድገት ፈተና ሆነው ከቀጠሉት […]