የመረጃ ጥራት ቁጥጥር አቅም ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ሰኔ 17/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተቋማዊ የመረጃ ጥራት ቁጥጥር አቅምን ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና ከተቋሙ የተለየዩ ስራ ክፍሎች ለተወጣጡት ከፍተኛ ባለሙያዎች ከስታቲስቲክ ኖርዌይ በመጡ በዘርፋ የተሻለ ልምድና ዕውቀት ባካበቱ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል። ስልጠናው ተቋሙ በስታቲስቲክስ መረጃ ጥራትና አቅርቦት ተወዳዳሪና በሂደትም የዘርፋ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የጀመረውን ጉዞ እውን ለማድረግ የሚያስፈልገውን የሰው ሀይል ለመፍጠር የጎላ ፋይዳ ያለው ሲሆን ስታቲስቲክ ኖርዌይ የተቋሙን የመረጃ ጥራት ቁጥጥር አቅም ግንባታና ሌሎች የሪፎርም ተግባራት እንዲሳኩ እገዛ እያደረጉ ከሚገኙ አለም አቀፍ ባላድርሻ አካላት መካከል አንዱ ነው።
የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት አጠቃቀም ላይ ስልጠና ተሰጠ

ሰኔ 16/2017ዓ.ም፣ ሶዶ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት (Integrated management system (IMIS)) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ 25 ሴክተሮች መስሪያ ቤቶች ለተወጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ። ተቋሙ ከተለያየ ምንጭ የሚሰበስባቸውን የስታቲስክስ መረጃዎችን በሳይንሳዊ ዘዴ በመተንተን ሪፖርቶቹን ተደራሽ ለማድረግ ጥቅም ላይ ካዋላቸው ዲጂታል የመረጃ ስርጭት መሳሪያዎች መካከል አንዱ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት (Integrated management system (IMIS) ሲሆን የስርዓቱ አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል። በዚሁ መነሻ ተቋሙ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮና ከክልሉ 25 ሴክተሮች ለተወጣጡ 100 ባለሙያዎች ስልጠና የሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ወደ ስራ ቦታቸው ሲመለሱ ያገኙትን ልምድና ዕውቀት የመረጃ አጠቃቀም ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ በክልሉ ለእቅድና ክትትል የስታቲስቲክስ መረጃን የመጠቀም ፍላጎትና ግንዛቤ በማሳደግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።
የስርዓተ ፆታና የአካል ጉዳተኞች ስታቲስቲክስ መመሪያ ዝግጅት ላይ ውይይት ተደረገ

ሰኔ 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስርዓተ ፆታና የአካል ጉዳተኞች ስታቲስቲክስ መረጃዎችን በጥናት፣ በቆጠራና በአስተዳደራዊ መዛግብት መረጃዎች ለማካተት የሚያስችል መመሪያ ላይ ከተቋሙ መሪ ስራ አስፈፃሚዎች ጋር ውይይት አደረገ። በውይይት መድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስነ-ሕዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይናለም ተሻገር የስርዓተ ፆታና የአካል ጉዳተኞች ስታቲስቲክስ የመረጃ ክፍተት መኖሩን ገልፀው ፤ ተቋሙ በሚያዘጋጃቸው የጥናትና ቆጠራ መረጃዎች ወጥና አለም አቀፍ ደረጃቸውን የጠበቁ የስርዓተ ፆታና የአካል ጉዳተኞች ስታቲስቲክስ መረጃዎች እንዲካተቱ ለማስቻል መመሪያው መዘጋጀቱን አንስተው ሁሉም ጥናትና ቆጠራ የሚያከናውኑ የስራ ክፍሎች ለመመሪያው ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች እንዲሰጡ የተዘጋጀ መሆኑን ገልፀዋል። የስርዓተ ፆታ፣ የአካል ጉዳተኝነት ስታቲስቲክስ መረጃዎችን ከጥናትና ቆጠራ በተጨማሪ ከሌሎች አማራጭ የመረጃ ምንጮች ከተቋማት፣ ከማህበረሰብ ክፍሎችና ከግለሰቦች ከሚሰበሰቡ መረጃዎች (citizen Generated data) ላይ ማግኘት እንደሚቻል ተጠቅሶ የተዘጋጁት መመሪያዎች በስራ ክፍሉ መሪ ስራ አስፈፃሚና ከፍተኛ ባለሙያዎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን ከተሳታፊዎች የተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች እንደግብዓት ተወስደዋል። በመድረኩ ማጠቃለያ የስነ-ሕዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይናለም ተሻገር የተነሱትን ሃሳብና አስተያየቶች በማካተት ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ተጨማሪ ውይይቶች ተደርገው መመሪያው ስራ ላይ እንዲውል ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።
የሪፎርም ትግበራን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ሰኔ 05/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የመንግስት አገልግሎት እና የአስተዳደር ሪፎርምን አስመልክቶ ለዋናው መስሪያ ቤት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ። ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው ተቋሙ መንግስት ያስቀመጠውን የሪፎርም ትግበራ ስራ አቅጣጫ ወደተግባር ለመቀየር የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጸው የዛሬው ስልጠና የዚሁ አካል እንደሆነና የተቋሙ የመንግስት አገልግሎት እና የአስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ስራዎችን አስመልክቶ የተከናወኑ ተግባራትንና ቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ከስልጠናው በቂ እውቀት በመያዝ ለተቋሙ የሪፎርም ስራዎች ስኬት የበኩላችሁን እንድታበረክቱ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመድረኩ በርካታ የሪፎርም ተግባራት ስራዎች አፈፃፀም በየደረጃው የቀረበ ሲሆን ከነዚህም መካከል የተቋሙ የሪፎርም ትግበራ ደረጃዎች ዝርዝር ፣ ህግና ስርዓቶች፣አሰራርና አደረጃጀት እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ሌሎች ርዕሶች ዙሪያ ተቋሙ በሪፎርም እየተገበራቸው ያሉ ስራዎችን በተቋሙ አመራሮች እና ባለሞያዎች ሰፊ ገለጻ ቀርቦ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።
የኦዲት አሰራርና መረጃ አያያዝ ላይ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ሰኔ14/2017 ዓ.ም አዳማ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የኦዲት አሰራርን አስመልክቶ በተለያዩ ርዕሶች ላይ ከዋናው መስሪያ ቤት እና ከቅርንጫፍ ለተወጣጡ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብነት ሃዋዝ ባደረጉት ንግግር ስልጠናው በኦዲት አሰራርና መረጃ አያያዝ የሰራተኛውን ክህሎት ለማጎልበት፤ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲሰጡ ባለሙያዎችን ለማብቃት ፤የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለማሳደግ የተዘጋጀ በመሆኑ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በንቃት በመሳተፍ በስልጠና የምታገኙትን ዕውቅት ተግባር ላይ እንድታውሉ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል። ስልጠናው ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ለቀጣይ ሁለት ቀናት በተለያዩ ርዕሶች ላይ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡
የአስተዳደራዊ መረጃ አሰባበብ፣ አያያዝና ትንተና ለማሻሻል የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

ሰኔ5/2017ዓ.ም ሀዋሳ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የአስተዳደራዊ መረጃ አመዘጋገብ፣ አያያዝና ትንተና ለማሻሻል የሚያስችል ስልጠና ለሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ሰጠ። በስልጠናውን መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ ልማትና ሜቶዶሎጂ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ የአስተዳደራዊ መዛግብት መረጃዎች ለስታቲስቲክስ መረጃ ግብዓት መሆናቸውን አንስተው እንደሀገር ያሉትን የመረጃ ክፍተቶች ለመሙላትና የክልሎችን አካውንት ለማዘጋጀት አስተዳደራዊ መረጃዎች ለኦፊሴላዊ ስታቲስቲክስ […]
የሪፎርም ትግበራን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ሰኔ 05/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የመንግስት አገልግሎት እና የአስተዳደር ሪፎርምን አስመልክቶ ለዋናው መስሪያ ቤት ሰራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።
የሁለተኛ ዙር የግብርና ቆጠራ አፈፃፀም ሪፖርት በበይነ መረብ (virtual meeting) ግምገማ ተደረገ

ሰኔ 2/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እያካሄደ በሚገኘው ሁለተኛ ዙር የግብርና ቆጠራ አፈፃፀም የተቋሙ ከፍተኛ አመራር ከ26ቱ ቅርንጫፍ ጽሀፈት ቤት ስራ አስፈፃሚዎች ጋር በበይነ መረብ (virtual meeting) በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተከናወኑ የግብርና ቆጠራ፣ የንግድ እርሻዎችና የበልግ ጥናት ተግባራትን ገምግሟል።
የሁለተኛ ዙር ግብርና ቆጠራ የስምንት ወራት የመስክ ስራ አፈፃፀም ተገመገመ

ግንቦት 26/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሁለተኛ ዙር የግብርና ቆጠራ የስምንት ወራት መስክ ስራ አፈፃፀም በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ተገመገመ። በመላ ሀገራችን እያተከናወነ የሚገኘው ሁለተኛ ዙር የግብርና ቆጠራ ያለፋት ስምንት ወራት መስክ ስራ አፈፃፀም ሪፖርት የተቋሙ ከፍተኛአመራርና የቆጠራው ቴክኒካል ኮሚቴ አባላት በተሳተፋበት መድረክ ቀርቦ በተደረገው ግምገማ የባለፋት ስምንት ወራት የመስክ ስራ አፈፃፀም በታቀደው መሠረት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ መሆኑ የተገመገመ ሲሆን በቀጣይ ወራት የሚከናወኑ ቀሪ የመስክ ተግባራት በተቀመጠላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ የስራ መመሪያ ተሰጥቶ የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል።
ለቆጠራ ካርታ ዝግጅት የGIS እና Advance Remote Sensing ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ሲሰጠ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

ግንቦት 25/2017ዓ.ም አዳማ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለተቋሙ የካርቶግራፊና ጂ አይ ኤስ ባለሙያዎች በካርታ ማካለል፣ GIS እና Advance Remote Sensing ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ሲሰጠ የቆየው የተግባር ስልጠና ተጠናቀቀ። በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር አብዱራዛቅ ዑመር የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለሀገራችን ልማት ዕቅድና ክትትል ግብዓት የሚሆኑ የስታቲስቲክስና ጂኦ ስፓሻል መረጃዎች የማቅረብ ሀላፊነት የተሰጣቸው ተቋማት በመሆናቸው በሁለቱም ተቋማት ያለውን ዕውቀትና ልምድ በተለየዩ አግባቦች ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመው በጋራ በመስራት ላይ እንዲሚገኙ አንስተው ለ15 ቀናት ሲሰጥ ቆይቶ ዛሬ የተጠናቀቀው ስልጠናም የቆጠራ ካርታ ማካለል ስራን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የGIS እና Advance Remote Sensing ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ያለውን ዕውቀትና ልምድ በተግባር ለማካፈል የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀው፤ ወደተቋማችሁ ስትመለሱ ያገኛችሁትን ስልጠና ተግባራዊ ለማድረግ በትጋት መስራት ይኖርባችኋል ሲሉ በስልጠናው ለተሳተፋት ባለሙያዎች መልዕክት አስተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው በተቋሙ የቆጠራ ካርታ ማካለል ስራ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት ስራውን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የባለሙያዎችን ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅም ለማሻሻል ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀው በቀጣይም በካርታ ዝግጅት፣ GISቴክኖሎጂና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተቋሙ ከስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት በጋራ እንደሚሰራ ገልፀዋል። የስልጠናው ተሳታፊዎችም ለስራቸው ጠቃሚ የሆነ የጽንሰ ሀሳብና የተግባር እውቀት እንዳገኙ ገልፀዋል።