በ2018 የሀገራዊ ልማት እቅድ ላይ ውይይት ተደረገ

ሐምሌ 16/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በ2018ዓ.ም ሀገራዊ የልማት እቅድ ላይ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ጋር ውይይት ተደረገ። የውይይት መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በሀገራችን በ2017 በጀት ዓመት በሁሉም ዘርፎች የተሻለ ውጤት የተመዘገበበት ዓመት መሆኑን አንስተው በ2018 በጀት ዓመት ቀጣይነት ያለው እድገት […]
ተቋማቱ በጋራ መስራት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረሙ

ሐምሌ 10/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በዓለም ባንክ ድጋፍ በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር በገጠር መንገድ ተደራሽነት ለምግብ ዋስትና ፕሮጀክት የሚሰሩትን የገጠር መንገድ ግንባታ ስራዎች መሰራታቸውን ለማረጋገጥ (Verification) የሚያስችል ስራ ለመስራት ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር ስምምነት ተፈራረመ። የስምምነት ሰነዱን የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ የትምጌታ አስራት እና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና […]
የ2018 የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የቅድመ አሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ሐምሌ 9/2017ዓ.ም አዳማ ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አግልግሎት በ2018ዓ.ም ለሚያካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የቅድመ አሰልጣኞች ስልጠና ከዋና መሠሪያ ቤትና 26ቱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተወጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018ዓ.ም የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ተግባራት እያከናወነ መሆኑን አንስተው ከነዚህ የቅድመ ዝግጅት ተግባር መካከል አንዱ […]
የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የቅድመ ዝግጅት ስራ ተጀመረ

ሐምሌ 8/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የቅድመ ዝግጅት ስራ መጀመሩን በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በተጋጀው የማስጀመሪያ ፕሮግራም ይፋ አደረገ። በቅድመ ዝግጅት ተግባራት የቆጠራው ስነ ዘዴ፣ የሰው ሀይል ዝግጅት፣ ለመስክ ስራ የሚውሉ ግብዓቶችና የቴክኖሎጂ ዝግጅት በዋናነት እንደሚከናወኑ የተገለፀ ሲሆን ይህን ስራ የሚያስተባብር ኮሚቴ ከዛሬ ጀምሮ እነዚህን ስራዎች […]
የስራ አፈፃፀም ግምገማ ተጠናቀቀ

ሐምሌ 5/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዋና መስሪያ ቤትና የ26ቱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ኃላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ የሚገኛው የ2017 ዓ.ም የተቋሙ ስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ሁለተኛ ቀን ውሎ በ2018ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጀ ለመጀመሪያ የሚካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ መሪ ዕቅድ ገለፃ በቢዝነስ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል። በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በ2017 ዓ.ም ስራ አፈፃፀም የተገኙትን ጠንካራ ተሞክሮዎችን አጠናክሮ በመቀጠልና የታዩትን ክፍተቶች በመፍታት በ2018ዓ.ም የተቋሙ ስራ ዕቅድ የሚከናዋኑ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ፣ የስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት፣ ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናትና የግብርና ቆጠራ ውጤት ሪፖርት ዝግጅት ተግባራትን በተሟላ መልኩ ለመሳካት በየደረጃው የሚገኘው የተቋሙ አመራርና መላው ሠራተኞች በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል።
ለተቋሙ የቀድሞ አመራር የሽኝት ፕሮግራም ተደረገ

ሐምሌ 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከጥቅምት 18/2015ዓ.ም እስከ ሰኔ 27/2017ዓ.ም ድረስ በኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ሲያገለግሉ ለቆዩትና ከሰኔ 25/2017ዓ.ም ጀምሮ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ለተሾሙት አቶ ሙሉቀን ቀሬ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የሽኝት ፕሮግራም ተደረገ። በተቋሙ ከፍተኛ አመራርና ሠራተኞች በተዘጋጀ የሽኝት ፕሮግራም ላይ የተገኙት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በረከት ፍስሀ ፅዮንና የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ በተቋሙ ቆይታቸው ለሰጡት የላቀ አመራርና ላሳዩት ትጋት ምስጋናቸውን አቅርበው ቀጣይ የስራ ጊዜያቸው የተሳካ እንዲሆን ምኞታቸውን ገልፀዋል።
የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ተደረገ

ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017በጀት ዓመት ያካሄዳቸው የጥናቶችና የቆጠራ ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ፣የዋናው መስሪያ ቤት እና የቅርንጫፍጽህፈት ቤት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተገመገመ። መድረኩን ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋማችን በ2017 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን የግብርና ቆጠራ፣ የስነ-ህዝብና ጤና ጥናትና ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት ሪፖርት ስንገመግም በሂደቱ የተገኙ ጥሩ ልምዶች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና በቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች በውይይቱ ተነስተው ልንማርባቸው እንደሚገባ አንስተው በስራው እስከአሁን በተገኘው ውጤት በከፍተኛ ትጋትና መነሳሳት ለሰሩ መላው የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም በዚህ ሂደት ውስጥ እገዛ ላደረጉ ሁሉም ባለደርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል። በበጀት ዓመቱ ሲከናወኑ የነበሩ የስነሕዝብና ጤና ጥናት፣ ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናትና የግብርና ቆጠራ የደረሱበትን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ገለፃ ቀርቦ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በነገው ዕለትም የውይይት መድረኩ ይቀጥላል።
የግብርና ቆጠራ ቀሪ ተግባራት ላይ ውይይት ተደረገ

ሐምሌ 2/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እያካሄደ በሚገኘው የግብርና ቆጠራ አፈፃፀምና ቀጣይ ስራዎች ላይ ከባለድርሻ አካካት ጋር ውይይት አደረገ። በውይይት መድረኩ መክፈቻ ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ የግብርና ቆጠራን በሚመለከት ከቆጠራው ቅድመ ዝግጅት ተግባራት አሁን እስክደረሰበት የስራው አፈፃፀም ድረስ የባለድርሻ አካላት ተሳትፎ ከፍተኛ ሚና እንዳለው አንስተው የዛሬው መድረክም ስራው የደረሰበትን አፈፃፀምና ቀጣይ ቀሪ ስራዎች ለመወያየት እንደሆነ ገልፀዋል። የግብርና ቆጠራ አጠቃላይ ሂደትና የደረሰበትን አፈፃፀም የሚያሳይ ገለፃ የቀረበ ሲሆን በቀረበው ገለፃና በቀጣይ የበልግ፣ የንግድ እርሻዎች መረጃ መሰብሰብና የሪፖርት ዝግጅት ተግባራት ላይ ውይይት ተደርጎበታል። በመድረኩ የተገኙት ባለድርሻ አካላትም ቆጠራው ጥሩ የሚባል አፈፃፀም ላይ መሆኑን ከቀረበው ሪፖርት መረዳታቸውን ተናግረዋል። በመድረኩ ማጠቃለያ የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በመድረኩ ለተገኙት ባለድርሻ አካላት ከቆጠራው ቅድመ ዝግጅት አሁን እስከደረሰበት አፈፃፀም ላደረጉት ተሳትፎ አመስግነው፤ ባለድርሻ አካላትን በማሳተፍ በጋራ መስራት ውጤታማ እንደሚያደርግ በማንሳት ቀጣይ ቀሪ ስራዎችንም በጋራ እንደሚሰሩ ገልፀው የውይይት መደረኩ ተጠናቋል።
የአስተዳደራዊ መዛግብት መረጃ አሰባሰብ፣ አያያዝና ትንተና ሂደቱን ለማሻሻል የሚያግዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከአስተዳደራዊ መዛግብት የሚገኙ መረጃዎችን እንደኦፊሴላዊ ስታቲስቲክስ መረጃ ለመጠቀም የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለተውጣጡ አመራሮችና ባለሙያዎች በክልሉ ዋና ከተማ ሰመራ እየተሰጠ ይገኛል። ስልጠናው ያስጀመሩት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አሊ መሀመድ በክልሉ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች የሚያመነጩትን የአስተዳደራዊ መረጃዎችን አሰባሰብ፣ አያያዝ፣አደረጃጀትና ትንተና ሂደቱን በማሻሻል እንደኦፊሴላዊ ስታቲስቲክስ መረጃ ለመጠቀም ስለመረጃዎቹ አስፈላጊነትና ያላቸው ጠቀሜታ ላይ በቂ ግንዛቤና መሠረታዊ ዕውቀት ያለው አመራርና ባለሙያ መፍጠር ቀዳሚ ተግባር እንደሆነ አንስተው ስልጠናው ከዚህ አንፃር የሚታያውን የሰው ሀይል የአቅም ክፍተቶችን በማሻሻል ከክልሉ የተለያዩ ሴክተር መሠሪያ ቤቶች የሚያመነጩትን የአስተዳደራዊ መረጃዎችን ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕቅዶች ግብዓትነት ለመጠቀም የሚያስችል የባለሙያዎችን አቅም ለመፍጠር የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አስረድተው የስልጠናው ተሳታፊዎች ወደየሴክተር መስሪያ ቤታቸው ሲመለሱ ያገኙትን እውቀትና ልምድ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠባቅበቸውም መልዕክታቸውን አሰተላልፈዋል። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ ሜቶዶሎጂና ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬከተር ክብርት ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ ስልጠናው በየሴከተሩ ያለውን የአስተዳደራዊ መረጃ አያያዝ ለማሻሻል የሚረዱ የስታቲስቲክ ፅንሰ ሀሳብና የቴክኖሎጂ አጠቀቃም ላይ በየክልሉ የሚገኙትን ባለሙያዎች አቅም በማሳደግ ከአስተዳደራዊ መዛግብት የሚገኙትን መረጃዎችን ጥራት በማሻሻል እንደአንድ ኦፊሴላዊ ስታቲስቲክስ መረጃ ለመጠቀም በተቋሙ ሪፎርም ትኩረት ተሰጥቶ በየክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙት ተግባራት አካል እንደሆነ ገልፀዋል። ስልጠናው በአስተዳደር መረጃዎች አመዘጋገብ፣አያያዝና የቴክኖሎጂ አጠቀቃም ላይ ለቀጣይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥ ከስልጠናው መርሀግብር ለመረዳት ተችሏል።
በዓመታዊ የስታቲስቲክስ መጽሄት ዝግጅት መነሻ ይዘት ላይ ውይይት ተካሄደ

ሰኔ24/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከተለያዩ ጥናቶችና የአስተዳደር መዛግብት የተገኙትን መረጃዎች በማደረጃትና አስፈላጊውን የጥራት ደረጃ በመከተል በሚያዘጋጀው ዓመታዊ የስታቲስቲክስ መጽሄት /statistical Abstract/ አካል በሆነው የ2016 ዓ.ም መፅሔት ዝግጅት መነሻ ይዘት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት አካሄደ። የውይይት መድረኩን ያስጀመሩት የተቋሙ የስነ-ህዝብ እና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይናለም ተሻገር ተቋሙ ከኢኮኖሚያዊ እና ከማህበራዊ ጥናቶች እንዲሁም ከተለያዩ የመንግስት መስሪያ ቤቶች የአስተዳደር መዛግብትየሚገኙትን መረጃዎችን በማሰባሰብ፣ በመተንተንና በማደራጀት በተለያዩ ፎርማት አዘጋጅቶ ለተጠቃሚዎች ተደራሽ ለማድረግ እያሰራ እንደሚገኝ አንስተው የስታቲስቲክስ መጽሄት /statistical Abstract/ በርካታ መረጃዎችን በአንድ ፎርማት አካቶ የሚይዝ በመሆኑ፤ ለፖሊሲ፣ ለልማት ዕቅዶች ዝግጅት እና ግምገማና ክትትል እንዲሁም ለልዩ ልዩ ምርምር ስራዎች እንደአንድ የመረጀ አማራጭ ያለው ፋይዳ የጎላ መሆኑን በማስረዳት፤ በዓመታዊ መጽሄት የሚካተቱ መረጃዎች ጥራት እንዲኖራቸው ከቅድመ ዝግጅት ሂደት ጀምሮ የመረጃዎቹን ምንጭ ከሆኑት ባለድርሻ አካላት ጋራ በተዘጋጀው የመጽሄቱ መነሻ ይዘት ዙሪያ ውይይት በማድረግ የሚገኙትን ተጨማሪ ግብዓቶችን ማካታት አስፈላጊ በመሆኑ የውይይቱ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልፀው ዓመታዊ መጽሄቱ በተቻለ መጠን የመረጃ ምንጭ የሆኑትን ተቋማት የመረጃ ፍላጎት ያማከለና ጥራቱ የተሟላ እንዲሆን ተሳታፊዎች ያላቸውን ሀሳብ በመስጠት የበኩላቸውን ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል ። በውይይቱ የዓመታዊ የስታቲስቲክስ መጽሄት ዝግጅት መነሻ ይዘት ገለፃ በተቋሙ ማህበራዊ አካቶ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ ከፍተኛ ባለሙያዎች ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በመድረኩ የተነሱ ሀሳብና አስተያየቶች እንደግብዓት በመውሰድ የውይይት መደረኩ ተጠናቋል።