ከባለድርሻ አካላት ጋር ውይይት ተደረገ

aa3a7246 2

ነሐሴ 1/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣በ2018ዓ.ም በሚያካሄደው የግብርና ናሙና ጥናትና ላይ ከብሔራዊ ቲክኒካል ኮሚቴ ጋር ውይይት ተደረገ።የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ዓመታዊ የግብርና ናሙና ጥናት የግብርና ቆጠራ በተካሄደበት ማግስት መካሄዱ በቆጠራው የተገኙ ግብዓቶችን በማካተት ጥራት ያለው የግብርና ናሙና ጥናት ለማከናወን እንደሚያግዝ ገልፀው፤የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የሚነሱ አስተያየቶችን እንደግብዓት ለመጠቀም ታስቦ መሆኑን ገልፀዋል። […]

የተቋሙ የዕውቀት ካፌ የማስተዋወቅ ፕሮግራም ተካሄደ

1t8a6029

ሐምሌ 30/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተቋማዊ እውቀትን ለማጋራት የሚያስችል የዕውቀት ካፌ የማስተዋወቅ ፕሮግራም ተካሄደ።ፕሮግራሙን በንግግር ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በተቋማዊ ሪፎርሙ ትኩረት ሰጥቶ በማከናወን ከሚገኘው ተግባራት ውስጥ አንዱ የዕውቀት አስተዳደር ስርዓትን መገንባት አገልግሎት ላይ ማዋል ሲሆን በዛሬው ዕለት የምናስተዋውቀው የዕውቀት ካፌ (knowledge cafe) […]

የዓለም አቀፍ ስነ-ሕዝብ ፈንድ (UNFPA) ለተቋሙ ድጋፍ አደረገ

1t8a5776.jpg

ሐምሌ 29/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የዓለም አቀፍ ስነ-ሕዝብ ፈንድ የኢትዮጵያ ቫይታል ስታቲስቲክስ መረጃ አሰባሰብና ሲቪል ምዝገባ ስርዓትን ለማዘመን እየተከናወኑ የሚገኙትን የሪፎርም ስራዎችን ለማጠናከር የሚያግዙ 17 ዴስክቶፕ ኮምፒውተሮች ድጋፍ ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አስረከበ። በርክክብ መርሀ ግብሩ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ መንግስት ዜጎች ከልደት እስከ ሞት የሚኖራቸውን መረጃ በአግባቡ በመሰብሰብ፣ በማደራጀትና […]

በ2018 ዓ.ም ለሚካሄደው የግብርና ናሙና ጥናት የአሰልጣኞች ስልጠና ተጀመረ

1t8a5575.jpg

ሐምሌ 28/2017ዓ.ም አዳማ፣የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየዓመቱ ከሚያካሂዳቸው የናሙና ጥናቶች አንዱ የሆነውን የ2018ዓ.ም ግብርና ናሙና ጥናት የመስክ ስራ የሚሰሩትን መረጃ ሰብሳቢዎች የሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ። በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የ2018ዓ.ም የግብርና ናሙና ጥናትን ከሁለተኛ ዙር ሀገር አቀፍ የግብርና ቆጠራ የመስክ ስራ በሚጠናቀቅበት ማግስት ማካሄድ ያስፈለገው በጥናቱ […]

ከፍተኛ አመራሩ ለክልሉ አመራር የስታቲስቲክስ ልማት ፕሮግራም እንዲሳካ የበኩሉን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪ አቀረበ

1t8a4869.jpg

የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በስታቲስቲክስ ልማት ዕቅድ ፕሮግራም እያከናወናቸው በሚገኙ ቆጠራዎችና ጥናቶች ላይ ለስራው መሳካት በሲዳማ ክልል ከሚገኘው የሀዋሳ ስታቲስቲክስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ጋር በቅርበት በመደገፍ ለሀገራዊ ስታቲስቲክስ ቆጠራዎች እና ጥናቶች መሳካት ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጥሩ ገልፀዋል:: በ2017ዓ.ም በክልሉ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትም ውጤታማ እንደነበሩ እና የክልሉ ድጋፍ አዎንታዊ […]

የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የክረምት በጎ አድራጎት ስራ አስጀመሩ

1t8a5472

ሐምሌ 26/2017ዓ.ም፣የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በሲዳማ ክልላዊ መንግስት ደቡብ ሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ መጬሾ የገጠር ቀበሌ በመገኘት የ2017ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት ስራ አስጀመሩ። በገጠረ ቀበሌው ተገኝተው የክረምት በጎ አድራጎት ስራውን ያስጀመሩት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክብርት ወ/ሮ ጥሩማር አባተ የዚህ ዓመት የበጎ አድራጎት ስራ ባለፋት ዓመታት ከተሰሩት በተለየ መልኩ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር […]

ለተቋሙ ከፍተኛ አመራር ደማቅ አቀባበል ተደረገ

1t8a4913.jpg 1

ሐምሌ 25/2017ዓ.ም ሀዋሳ፣የ2017 ዓ.ም የክረምት በጎ አድራጎት ተግባራት ለማከናዋን ወደ ሲዳማ ክልል ለተጓዘው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራር የሲዳማ ክልል የፕላንና ልማት ቢሮ ሀላፊ ዶ/ር አራርሶ ገረመውና በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሀዋሳ ስታቲስቲክስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አሰጋሽ አሰፋ በሀዋሳ አየር ማረፊያ ተገኝተው ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል። ከፍተኛ አመራሩ ነገ ሐምሌ 26/2017ዓ.ም በሲዳማ ክልል ደቡባዊ […]

ተቋማቱ የአንድ ጀምበር የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዱ

g92a6125

ሐምሌ 24/2017ዓ.ም ለገጣፎ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል በሀገር አቀፍ ደረጃ በአንድ ጀምበር 700 ሚሊየን የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር በሸገር ከተማ በለገዳዲ ለገጣፎ ክፍለ ከተማ የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር አካሄዱ። መርሀ ግብሩን በንግግር ያስጀመሩት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በሀገራችን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር መካሄድ ከጀመረበት ጊዜ […]

የ2017ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተካሄደ

1t8a4233.jpg

ሐምሌ 17/2017ዓ.ም አዳማ፣የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በምስራቅ ሸዋ ሎሜ ወረዳ የችግኝ ተከላ አካሄዱ። መርሀግብሩን ያስጀመሩት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በባለፉት ሰባት ዓመታት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ አመራር ሰጪነት የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ዘመቻ ስራ ሳይቆራረጥ […]

በ2017 በጀት ዓመት ተቋሙ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡ ተገለፀ

1t8a4034.jpg

ሐምሌ 16/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በመካከለኛ ዘመን (ከ2016-2018ዓ.ም) በስታቲስቲክስ ልማት ዕቅድ ለማሳካት ከታቀዱት አራት ትላልቅ ተግባራት ሶስቱን ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለፀ። በ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና 2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ለመወያየት የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በተገኙበት መድረክ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት (ከ2016-2018ዓ.ም) ለማሳካት ካቀዳቸው ተግባራት መካከል የኢትዮጵያ ስነ-ህዝብና ጤና […]