የፍልሰት መረጃ ለማጋራት የተፈረመው መግባቢያ ሰነድ ትግበራ ላይ ውይይት ተደረገ

ነሐሴ 20/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የፍልሰት መረጃ ለማጋራት ከዚህ ቀደም በብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት መካከል የተፈረመው መግባቢያ ሰነድ ትግበራ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ ተጀመረ። የኢትዮጵያ መንግስት ፍልሰትን ለማስተዳደር ብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት አቋቁማ በመስራት ላይ እንደምትገኝ የገለፁት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሀገራዊ የፍልሰት የመረጃ ፍላጎትን ለማሟላት […]
የኢትዮጵያ ስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ሪፖርት ዝግጅት ላይ የቴክኒክ ኮሚቴው ውይይት አደረገ

ነሐሴ 19/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ አምስተኛ ዙር የኢትዮጵያ ስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ሪፖርት ዝግጅት ለቴክኒክ ኮሚቴ ቀርቦ ጋር ውይይት ተደረገበት። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የተቋሙ የዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው ስራው በቴክኒክ ኮሚቴውና በሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ዛሬ ያለበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ምስጋናቸውን በማቅረብ የውይይት መድረኩን አስጀምረዋል። የስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ሪፖርት ዝግጅት በስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት […]
የኢትዮጵያ ስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ሪፖርት ዝግጅት ላይ ውይይት ተደረገ

ነሐሴ 12/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣አምስተኛ ዙር የኢትዮጵያ ስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ሪፖርት ዝግጅት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋና የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደረገበት። በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ ስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት በተቋማችን አመራሮችና ሰራተኞች፣ በመንግስትና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ትጋትና […]
የግብርና ናሙና ጥናት የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ

ነሐሴ 7/2017ዓ.ም አዳማ፣የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ላለፉት 10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የግብርና ናሙና ጥናት የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።የስልጠናው ማጠቃለያ መድረክ ላይ የተገኙት የተቋሙ የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው በስልጠናው ለተሳተፉ ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኛችሁትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም በቀጣይ ለመረጃ ሰብሳቢዎች የምትሰጡትን ስልጠና በአግባቡ በማሰልጠን ጥራት ያለው መረጃ የመሰብሰብ ዕቅዱ እንዲሳካ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባችው የስራ መመሪያ […]
ለኮሪያ ስታቲስቲክስ ልዑክ የጉብኝት ፕሮግራም ተዘጋጀ

ነሐሴ 6/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣የኮሪያ ስታቲስቲክስ ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የቱሪስት ማዕከላትን እንዲጎበኙ ተደረገ። በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ የሚገኘው የኮሪያ ስታቲስቲክስ ልዑካን ቡድን በአዲስ አበባ የቱሪስት ማዕከላትን እንዲጎበኙ በተቋሙ በተዘጋጀ ፕሮግራም አድዋ ሙዚየም፣ ወዳጅነትና እንጦጦ ፓርክን ጎበኙ። በጉብኝቱ ወቅት በፓርኮችና በከተማ ውስጥ ባዩት ሁሉ ደስተኛ መሆናቸውን የከተማዋን ዋና የቱሪስት መዳረሻዎች በማወቃቸው […]
የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የአሰልጣኞች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

ነሐሴ 7/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018ዓ.ም ለሚካያሂደው የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ሁለተኛ ዙር የአሰልጣኖች ስልጠና በ13 የስልጠና ማዕከላት መሰጠት ተጀመረ። ስልጠናውን ከዋናው መስሪያ ቤት በበይነ መረብ ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በመካከለኛ ዘመን የስታቲስቲክስ ልማት ፕሮግራም ለማከናወን ካቀዳቸው ጥናቶችና ቆጠራዎች መካከል በ2017ዓ.ም ሁለት ጥናቶችና የግብርና ቆጠራ በተለየ ትኩረትና […]
ለ13 የስልጠና ማዕከላት የስራ ኦረንቴሽን ተሰጠ

ነሐሴ 6/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ሁለተኛ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና ለሚሰጥባቸው 13 የተመረጡ ዩኒቨርስቲዎችና እንዲሁም የክልል መንግስት የትምህርት የቴክኒክና ሙያ የስልጠና ማዕከላትና የተቋሙ የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊዎች ስልጠናውን ለማሳካት የሚጠበቅባቸው ኃላፊነት ላይ ኦረንቴሽን ተሰጠ። የስራ ኦረንቴሽኑን በበይነ መረብ የሰጡት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የተሟላ ስልጠና ለመስጠት ከየማዕከላቱ ስለሚጠበቅባቸው ተግባራት የስራ […]
ለኮሪያ ስታቲስቲክስ ልዑካን ቡድን ስለተቋሙ ገለጻ ተደረገ

ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ለመስጠት ወደ ኢትዮጵያ ለመጡት የኮሪያ ስታቲስቲክስ ልዑካን ቡድን ስለተቋሙ ግንዛቤ ማስጨበጫ ገለጻ ተደረገ። የልዑክ ቡድኑን ለመቀበል በተዘጋጀው ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የተቋሙ ከምስረታው ጀምሮ አሁን እስከ ደረሰበት ደረጀ ያለፈባቸውን ተቋማዊ ጉዞ፣ በሂደቱም የተገኙ ውጤቶች እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጨ ላይ ገለፃ ያቀረቡት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ […]
የኮሪያ ስታቲስቲክስ ለተቋሙ ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል

ነሐሴ 5/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትና ኮሪያ ስታቲስቲክስ በሰው ሀይል አቅም ግንባታ ላይ በትብብር ለመስራት ከዚህ ቀደም የተፈራረሙት የጋራ ስምምነት አካል የሆነውን የአቅም ግንባታ ስልጠና ከኮሪያ ስታቲስቲክስ በመጡት ባለሙያዎች በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት መሰጠት ተጀመረ። በፕሮግራሙ መክፈቻ ላይ ተገኝተው ስልጠናውን ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ባከር ሻሌ ኢትዮጵያና ኮሪያ ያላቸው ግንኙነት ከልማት […]
ለሁለተኛ ዙር የአሰልጣኞች ስልጠና አስተባባሪዎች የስራ መመሪያ ተሰጠ

ነሐሴ 2/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018ዓ.ም ለሚካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ በ13 የስልጠና ማዕከላት ከነሐሴ 7/2017ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የአሰልጣኞች ስልጠና ለማስተባበር ከዋናው መስሪያ ቤት ወደ ማዕከላቱ ለተመደቡት 80 ባለሙያዎች የስራ መመሪያ ተሰጠ። በመድረኩ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ በ2017ዓ.ም በተሰሩት ትላልቅ ሀገራዊ ጥናቶችና ቆጠራ የተገኙትን መልካም ተሞክሮዎች በማስቀጠል እንደክፍተት የታዩትን […]