የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመረጃ ሰብሳቢዎች ስልጠና መሰጠት ተጀመረ

መስከረም 5/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚያካሂደው የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ስራ የሚሰማሩ መረጃ ሰብሳቢዎች፣ ተቆጣጣሪዎችና ስታቲሺያኖች በአዲስ አበባና በሁሉም ክልሎች በተዘጋጁ ከ53 በላይ የስልጠና ማዕከላት መስጠት ተጀመረ። የስልጠናው ዓላማ ለሀገራችን የኢኮኖሚ ዘርፍ የጎላ ፋይዳ ያላቸውን ስታቲስቲክስ መረጃዎች በጥራት በመሰብሰብ ለሚፈለገው ዓላማ ማዋል የሚያስችል የሰው ሀይል ለማዘጋጀት ታስቦ የሚሰጥ እንደሆነ በአዲስ አበባ […]
ለመረጃ ሰብሳቢዎች ስልጠና አስተባባሪዎች ኦረንቴሽንና የስራ ስምሪት ተሰጠ

መስከረም 2/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018ዓ.ም ለሚካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ በ54የስልጠና ማዕከላት ከመስከረም 5/2018ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠውን የመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ስልጠና ለማስተባበር ከዋናው መስሪያ ቤት ወደ ማዕከላቱ ለተመደቡት ባለሙያዎች ኦረንቴሽንና የስራ ስምሪት ተሰጠ። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ከ2016 -2018 ዓ.ም በስታቲስቲክስ ልማት ፕሮግራም ታቅደው እየተከናወኑ ያሉ ትላልቅ ስራዎችን ማሳካት የቻልነው ቁርጠኛ በሆነ […]

ጳጉሜ 4/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ከሸገር ከተማ ለገጣፎ ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የባህል ቡድን በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት በጎቤና ሽኖዬ ባህላዊ ጭፈራ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል። የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ወጣቶቹ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ለመግለጽ ወደተቋማቸው በመምጣቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የአንድነት፣ የመቻቻልና […]
ለኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የቆጠራ ቦታ ካርታ በታብሌት የመጫን ስራ እየተከናወነ ይገኛል

ጳጉሜ 4/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ለአዲስ አበባ ቅ/ጽ/ቤት ለኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የሚያስፈልጉ 6,332 ታብሌቶች ላይ የቆጠራ ቦታ ካርታ የመጫን ስራ እየተከናወነ ይገኛል። የቆጠራ ቦታ ካርታ መረጃ ሰብሳቢዎችበመስክ የሚሰሩበትን የስራ ቦታቸውን ለይተው እንዲያውቁ ከማድረጉም በላይ የስራ ድግግሞሽ እንዳይኖር የሚያስችል አስፈላጊ ግብዓት ነው። በቀጣይም ይህ ተግባር በ25ቱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤትና አንደ ልዩ ክላስተር እንደሚቀጥል ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል።
ለኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለመስክ ስራ ፍሬሚንግ የሚያስፈልጉ አስተዳደራዊ መረጃ አቅርቦት ላይ ስልጠና ተሰጠ

ጳጉሜ 1/2017ዓ.ም አዳማ፣ የኢትዮጵያ ስትቲስቲክስ አገልግሎት ከፌዴራል ፣ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና ከሁሉም ክልል ፕላንና ልማት፣ የንግድና ገበያ ልማት ፣ ከገቢዎች፣ ከኮንስትራክሽንና ከኢንዱስትሪ ቢሮ ለተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በ2018 ዓ.ም ለሚካሄደው የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለፍሬሚንግ ግብዓትነት የሚውሉ አስተዳደራዊ መረጃ አቅርቦት ላይ ስልጠና ተሰጠ። ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በ2018 የኢኮኖሚ ድርጅቶች […]
በ13ቱ ማዕከላት የተሰጠው የመረጃ ሰብሳቢዎች የቅጥር ፈተና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል
ነሐሴ 27/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ13 ማዕከላት ለአዲስአበባ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመረጃ ሰብሳቢዎች ቅጥር ፈተና በስኬት መጠናቀቁን ከሁሉም የፈተና ማዕከላት በደረሰን መረጃ ለማረጋገጥ ተችሏል። ለፈተናው የተመረጡ 7,500 የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ወጣቶች ተሳትፈዋል። ለፈተናው መሳካት በተለያየ መልኩ እገዛ ላደረጋችሁ በመሉ ተቋማችን ከፍተኛ ምስጋና ያቀርባል።
የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለመረጃ ሰብሳቢዎች ፈተና ለሚሰጠው ግብር ሀይል ኦረንቴሽንና ስምሪት ተሰጠ

ነሐሴ 27/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በአዲስአበባ13 ማዕከላት ለኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመረጃ ሰብሳቢዎች ሙያ ለሚቀጠሩ ሰራተኞች ፈተና ለሚሰጠው ግብር ሀይል ኦረንቴሽንና ስምሪት ተሰጠ። የኦረንቴሽንና ስምሪት መድረኩ ላይ በፈተናው ሲስተም ላይ ከስራና ክህሎት ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ስራ ገበያ መረጃ ሥርዓት (LMIS) በመጡ የቴክኒክ ባለሙያዎች ኦረንቴሽንና ገለፃ ተሰጥቷል።
በአዲስ አበባ ቅ/ጽህፈት ቤት ስር ሲሰጥ የቆየው ሁለተኛ ዙር የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ

ነሐሴ 24/2017ዓ.ም አዲስአበባ፣በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የአዲስ አበባ ቅ/ጽህፈት ቤት ስር ሲሰጥ የቆየው የሁለተኛ ዙር የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ። በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የአዲስአበባ ቅ/ጽህፈት ቤት ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሰማ ኡርጌሳ በስልጠና ለተሳተፋት ሰልጣኞች ስልጠናውን በሚገባ ተከታትላችሁ በማጠናቀቃችሁ እንኳን ደስ አላቹ በማለት ያላቸውን ምኞት ገልጸው በስልጠናው በቂ ዕውቀትና ልምድ እንዳገኛችሁ የሚታመን […]
ለተቋሙ ባለሞያዎች መረጃ የማጥራትና የሪፖርት ዝግጅት ክህሎት ለማሳደግ የሚያግዝ ሥልጠና ተሰጠ

ነሐሴ 23/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለተወጣጡ ባለሞያዎች “Monetary Welfare and Poverty Measurement” በሚል ርዕስ የተዘጋጀ ሥልጠና ተሰጠ። በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በተቋሙ እየተካሄደ ላለው ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት (NIHS) የመረጃ ማጥራትና ሪፖርት ዝግጅት ክህሎት ለማሻሻል ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑን ገልጸው፤ በሥልጠናው ያገኛችሁትን […]
የቀድሞ የተቋሙ ሰራተኞች የቆጠራ ስራ ላይ እንዲሳተፉ ጥሪ ተደረገላቸው

ነሐሴ 23/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የቀድሞ የተቋሙ ሰራተኞች የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ስራ እንዲሳተፉ ጥሪ ተደረገላቸው። ለቀድሞ የተቋሙ ሰራተኞች እንኳን በሰላም ወደቤታችሁ መጣችሁ ያሉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በተቋሙ ቆይታችሁ ያፈራችሁትን ዕውቀት፣ ክህሎትና ልምድ አሁን ላሉት ወጣት የስታቲስቲክስ ባለሙያዎች እንድታካፍሉና ለዚህ ትልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክት ስኬት የድርሻችሁን እንድታበረክቱ ታስቦ የተደረገ […]