የብሔራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓት ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል

ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በብሔራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓት ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተቋሙ ከፍትኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል። የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤቢሳ አሰፋ የብሔራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓት አዋጅ ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማ የሀገሪቱን መረጃ የማመንጨት ስትራቴጂና ፕሮግራሞችን ህጋዊና ወጥነት ባለው መልኩ በመምራት የሀገሪቱ የልማት ፕሮግራሞች […]
የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) ለተቋሙ ድጋፍ አደረገ

ጥቅምት 14/02/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለስታቲስቲክስ መረጃን ዝግጅት የሚያግዙ የአይ ቲ (IT) ዕቃዎች ድጋፍ አደረገ። በርክክብ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ወቅታዊና ጥራቱን የጠበቀ የስራ ስምሪትና የፍልሰት መረጃዎችን ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች በማሰባሰብና ተንትኖ ጥቅም ላይ ለማዋል እየሰራ መሆኑን ገልፀው ዛሬ […]
የተቋሙ ድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ተባብረው የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገለፁ

ጥቅምት 13/2018 አዲስ አበባ፣የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የዋና መስሪያ ቤት የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ተባብረው የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገለፁ:: በዚሁ አጭር የጋራ መድረክ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር የሁላችንም የጋራ ግብ የመረጃ ጥራት እውን ማድረግ የሚያስችለን ርብርብ ነው ሲሉ ሰራተኞቹን አመስግነው ይህ መነሳሳት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ ብለዋል:: ሰራተኞቹም በበኩላቸው የተቋሙን አሳታፊ እና አበረታች መልካም ጅምር አመስግነዋል:: […]
የተቋሙ ሪከርድና ማህደር የስራ ክፍል በአዲስ መልክ ታድሶ አገልግሎት መስጠት ጀመረ

ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት የሪከርድና ማህደር የስራ ክፍል በአዲስ መልክ ታድሶ አገልግሎት መስጠት ጀመረ። የሪከርድና ማህደር ክፍል ሰራተኞችለስራ ፍፁም ምቹ ያልነበረውን የስራ ክፍል ለሀገሪቱ ተመሳሳይ ተቋማት ሞዴል መሆን በሚችል ደረጃ ለሠራተኞችና በክፍሉ ለሚሰጠው አገልግሎት ምቹ ሆኖ እንዲታደስ ለሰሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ምስጋናቸውን አቅርበዋል። የስራ ክፍሉ […]
የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመስክ ስራ ለሚደግፉ ባለሙያዎች የስራ ስምሪት ተሰጠ

ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባየኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመስክ ስራን በተቋሙ 26ቱ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ላይ ሆኖ በቅርበት ድጋፍ ለመድረግ ከዋና መስረቤት ወደ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ለሚላኩ ባለሙያዎች የስራ ስምሪት ተሰጠ። በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በመላ ሀገሪቱ 55 የስልጠና ማዕካለት ሲሰጥ የቆዬውን የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመረጃ ሰብሳቢዎች፣ የስታቲስቲሺያኖች […]
የ2018ዓ.ም የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመስክ ሰራተኞች ስልጠና ተጠናቀቀ

መስከረም 28/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ላለፉት 25 ቀናት በመላ ሀገሪቱ በ56 የስልጠና ማዕከላት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመስክ ሰራተኞች ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል። ለስልጠናው መዝጊያ ፕሮግራም ከማዕከል በቪዲዮ መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመረጃ ሰብሳቢዎች፣ ተቆጣጣሪዎችና ስታቲስቲሺያኖች ስልጠና በታቀደው መሰረት የሚፈለገውን የዕውቀት ክህሎትና […]
ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት የመስክ ስራ ተጠናቀቀ

መስከረም 27/2018 ዓ.ምየኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከመስከረም 10/2017ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመት ከመላ ሀገሪቱ ገጠርና ከተማ በተመረጡ 2,881 የቆጠራ ቦታዎች ሲካሄድ የነበረው ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት የመስክ ስራ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁ ተገለፀ። የመስክ ስራ መጠናቀቁን በማስመልከት በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በተሰጠው መግለጫ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የጥናቱ የመስክ ስራ በታቀደው መሰረት እንዲጠናቀቅ […]
በተቋማቱ መካካል የልምድ ልውውጥ መርሀ-ግብር እየተደረገ ይገኛል

መስከረም 26/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017ዓ.ም ባካሄደው የግብርና ቆጠራ የተገኙትን ልምዶች ለናሚቢያ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ የማካፈል የስልጠና መርሀ-ግብር በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት እየሰጠ ይገኛል። በመድረኩ ተገኝተው የእንኳን ደህና መጣችሁ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የግብርና ዘርፍ ስታቲስቲክስ መረጃዎች ከአመታዊ የግብርና ናሙና ጥናት በመሰብሰብ፣ በማጠናቀርና ሪፖርት አዘጋጅቶ ለመንግስትና ለሌሎች […]
የስነ- ህዝብና ጤና ጥናት የሪፖርት ዝግጅት ተጀመረ

መስከረም 20/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስነ – ህዝብናጤና ጥናት የመጨረሻ ሪፖርት ዝግጅት ስራ ከቴክኒክ ኮሚቴና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የሪፖርት ዝግጅት ስራ ጀመረ።
የተቋሙ የሪፎርም ሥራዎች ተጎበኙ

መስከረም 12/2018 ዓ.ምበኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ሦስት ዓመታት የተሠሩት ሁሉ አቀፍ ተቋማዊ ሪፎርም ሥራዎች በክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በተመራው የሥራ ቡድን ተጎበኘ፡፡ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተቋማዊ ሪፎርም የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን የተገኙት ውጤቶች በሚመለከት ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን የተቋማቸው አመራርና መላው ሠራተኛ ተቋሙን የዘርፉ […]