በUNFPA የተቋሙ የመረጃ ስርጭት አማካሪ ባለሙያ ጋር በመተባበር “The Information and Data Management System (IRIS) Module of Renata 7” ላይ ለተቋሙ የስታቲስቲክስ መረጃ ስርጭት ባለሙያዎች የዕውቀት ሽግግር ስልጠና በተቋሙ ዋና መስራቤት የስልጠና ማዕከል እየተሰጠ ይገኛል።
የ2019 ዓ.ም ግብርና ናሙና ጥናት የአሰልጣኞች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል ።

ሐምሌ 15/11/2018 ዓ.ም ባቱ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በየዓመቱ የሚያካሄደው የግብርና ናሙና ጥናት የቅድመ ዝግጅት ተግባራት አካል የሆነው የመረጃ ሰብሳቢዎች አሰልጣኝ ስልጠና በባቱ ከተማ በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ እየተሰጠ ይገኛል። በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ም/ዋ/ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ የ2019 ዓ.ም የግብርና ናሙና ጥናት ለማካሄድ የሚደረጉት የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በሀገራችን ሁለተኛ ዙር ግብርና ቆጠራ […]
34ተኛ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ባለሙያዎች ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

ሐምሌ 11/11/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ባለሙያዎች ማህበር 34 ተኛ ዓመታዊ ጉባኤ ” The role of statistics methods for strengthening digitalization to implement ethiopias development plan” በሚል መሪ ሀሳብ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል ። በጉባኤው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዲጂታላዜሽን ዘርፍ ም/ዋ/ዳይሬክተር ክብርት ዶክተር ሜሮን ክፈለው በሀገራች ብቁ […]
በሀዋሳ ስታቲስቲክስ ቅ/ጽ/ቤት የተሰሩ ስራዎች ተጎበኙ

ሐምሌ 9/11/2018 ዓ.ም ሀዋሳ በኢትዮትጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የመካከለኛ ዘመን (2016_ 2018 ዓ.ም) የስታቲስቲክስ ልማት ዕቅዶች አፈፃፀምና በ2019 ዓ.ም የዕቅድ ዝግጅት ላይ በሀዋሳ ከተማ ሲመክሩ የቆዩት የተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ሀብትን መልሶ ለአገልግሎት በማዋልና ምቹ የስራ ቦታ ለመፍጠር የተሰሩ የሪፎርም ስራዎችን ጎበኙ፡፡ በሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች ለሌሎች ቅ/ጽ/ቤቶች እና በቀጣይ ለሚሰሩት ተመሳሳይ […]
በሀዋሳ ከተማ የተቋሙ ዓመታዊ የስራ አፈጻጸም ጉባኤ ላይ ሲሳተፉ የቆዩት የተቋሙ ከፍተኛና መካካለኛ አመራሮች በሀዋሳ ታቦር ተራራ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።

ሐምሌ 9/11/2018 ዓ.ም ሀዋሳ
በተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ላይ ያተኮረ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ሐምሌ 7/2018 ዓ.ም ሀዋሳ ለኢትዮትጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አመራሮችና ከፍተኛ ባለሙያዎች ዕምርታ በስታቲስቲክስ ልማት በሚል ርዕስ በተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ላይ አተኩሮ በተዘጋጀው ሰነድ ላይ ስልጠና በሀዋሳ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የ 2018 ዓ.ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀምና የ 2019 ዓ.ም ዕቅድ ዝግጅት ላይ የሚመክር ዓመታዊ ጉባኤ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ይገኛል፡፡

ሐምሌ 6/2018 ዓ.ም ሀዋሳ፣
ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አካላት ጋር ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ሐምሌ 4/2018 ዓ.ም ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከሁሉም ክ/ከተማ ከተወጣጡ ስራ አስፈጻሚዎችና የፕላን ጽ/ቤት ሀላፊዎች ጋር በከተማው እያተከናወነ የሚገኘው የቆጠራ ካርታ አብዴቲንግ የመስክ ስራ ሪፖርት ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት ተደረገ። በውይይቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው በከተማው እየተከናወነ የሚገኘው የቆጠራ ካርታ ወቅታዊ የማድረግ ስራ በከተማው […]
የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጫ ጥናት የመስክ ስራ ተገመገመ

ሐምሌ 3/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እያከናወነ የሚገኝው የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጫ ጥናት የመስክ ስራ በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት የስብሰባ አዳራሽ ተገመገመ፡፡በግምገማው መድረክ የ20 የመስክ ስራው አስተባባሪዎች ሪፖርትና የማህበራዊና አካቶ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጥሩዘር ተናኜ ማጠቃለያ ሪፖርት ቀረቦ ውይይት ተደርጓል፡፡ በግምገማው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት የተቋሙ የስነ ህዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና […]
ብሔራዊ የምርምር ልማት ወጪ ጥናት ለማካሄድ የሚያስችል ውይይት ተካሄደ

ሰኔ 26/10/2018 አዳማ የኢትዮትጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፌደራል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጋር በጋራ በሚያካሄዱት ብሔራዊ የምርምር ልማት ወጪ ጥናት ላይ ከባለድርሻ አካት ጋር በአዳማ ከተማ ውይይት እያካሄደ ይገኛል፡፡ መድረኩን በንግግር የከፈቱት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ባይሳ በዳዳ የምርምር ልማት ለአንድ ሀገር ዕድገት መሰረታዊ ጉዳይ መሆኑን አስረድተው ቀጣይ ለሚሰሩ የምርምር ልማት ስራዎች የዘርፉ አሁናዊ […]