የደቡብ ሱዳን ስታቲስቲክስ ቢሮ ዋና ዳይሬክተር ተቋሙን ጎበኙ

ሰኔ 25/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የደቡብ ሱዳን ስታቲስቲክስ ቢሮ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኡጉስቲኖ ቲንግ (Augustino Ting /Ph.D.) በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ ዳይሬክተሩ በተቋሙ የተሰሩ የሪፎርም ተግባራትን የጎበኙ ሲሆን ባደረጉት ጉብኘት ለተቋማቸው የሚሆኑ ልምድና ግንዛቤ እንዳገኙ ገልጾው ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋማቸው […]
የተወካዮች ምክር ቤት የስታቲስቲክስ አዋጅን አጸደቀ፡፡

ሰኔ 23/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የልማት ዕቅድን፣ የፖሊሲ ቀረፃንና ብሔራዊ ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራሞችን የመረጃ ፍላጎትን ለማሟላት እንዲያስችል የተዘጋጀው አዲሱ የስታቲስቲክስ አዋጅ ዛሬ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ፀድቋል፡፡ የፀደቀው የአዲሱ የስታቲስቲክስ አዋጅ በብሔራዊ የስታቲስቲክስ ስርዓት የባለድርሻ አካላትን ሚና እና ኃላፊነት የሚደነግግ፣ ሞያዊ ነፃነትን የሚያረጋግጥ፣ ተቋማዊ አቅምን የሚያጠናክር እንዲሁም ተስማሚ የሆኑ ደረጃዎች፣ ምደባዎችን፣ ሜታ ዳታዎችን እና የስታቲስቲክስ ስርዓቶችን በመጠቀም […]
ለሐረሪ ክልል ሴክተር መስሪያ ቤቶች በስቲታስቲክስ መረጃ ጥራትና አያያዝ ላይ ስልጠና ተሰጠ

ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ድሬድዋ ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከሐረሪ ክልል ፕላን ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከክልሉ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በስታቲስቲክስ መረጃ አያያዝና ጥራት ላይ በድሬድዋ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡ በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስታቲስቲክስ ሜቶዶሎጂና ሲስተም ልማት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ ተቋማቸው ክልሎች የሚያመነጩትን መረጃ አያያዝና ጥራት ለማሻሻል […]
9ኛው የተባበሩት መንግስታት ቢዝነስና የንግድ ስታቲስቲክስ የባለሙያዎች ስብሰባ ተጠናቀቀ

ሰኔ 18/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ ላለፋት ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ሲካሄድ የቆየው 9ኛው የተባበሩት መንግስታት ቢዝነስና የንግድ ስታቲስቲክስ ባለሙያዎች ስብሰባ ተጠናቋል፡፡ በመድረኩ መክፈቻ ላይ ተገኘተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋማቸው ወቅታዊ እና ጥራቱን የጠበቀ የቢዝነስና የንግድ ስታቲስቲክስ ለፖሊሲ አውጪዎች እያቀረበ እንደሚገኘ አስረድተው በዚህ ስብሰባም ከዘርፉ ባለሙያዎች የሚቀርቡትን የተሻሉ […]
የሲቪል ሰርቪስ ዲጂታል አገልግሎት አሰጣጥ ኤግዚቢሽን ተጎበኘ

ሰኔ 15/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፍተኛ አመራሮች፤ ዋና መስሪያ ቤት አመራሮች እና ሠራተኞች ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በዲጂታል ቴክኖሎጂ አገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያዘጋጀውን ኤግዚቢሽን ጎበኙ። ኤግዚቢሽኑ ተቋማችን እያካሄደ ከሚገኘው ዲጂታል ስታቲስቲክስ ሪፎርም ተግባራት ጋር የሚመጋገብ በመሆኑ ጥሩ ልምድና ግንዛቤ የተገኘበት ኤግዚቢሽን እንደሆነ ተሳታፊዎቹ ገልጸዋል፡፡ በኤግዚቢሽኑ የቀረቡት ቴክኖሎጂዎች ባነሰ ወጪ፤ በአጭር ጊዜ ቀልጣፋ አገልግሎትን መስጠት […]
የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች መረጃ የማረጋገጥ የመጀመሪያ ዙር የመስክ ስራ አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ

ግንቦት 28/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር እያካሄደ በሚገኘው የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች መረጃ የማረጋገጥ ስራ የመጀመሪያ የመስክ ስራ አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ። በመድረኩ ተገኝተው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የስነ ህዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ አይናለም ተሻገር የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች መረጃ ማረጋገጥ የመስክ ስራ ለመደገፍ ከዋናው መስሪያ ቤት ወደቅርንጫፍ ጽህፈት […]
ተቋሙ እየተጠቀመባቸው በሚገኙ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስርዓቶች ላይ ለአይሲቲ ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

ግንቦት 27/2018 ዓ.ም አዳማ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እየተገበራቸው በሚገኙ የዲጂታል ቴክኖሎጂ ውጤቶች ላይ ከ26ቱ የስታቲስታክስ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት ለተውጣጡ የአይቲ ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል። የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤቢሳ አሰፋ ተቋማችን ዲጂታል ቴክኖሎጂ በመጠቀም ቆጠራና ጥናቶችን ጥራትንና ወቅታዊነት ለማስጠበቅ በሰፊው እየሰራ የሚገኝ መሆኑን እና በድጋፍ ዘርፉም መንግስት ባለማቸው ዲጂታል […]
በተቋሙ የስራ ጉብኝት ተደረገ

ግንቦት 27/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን ከፍተኛ አመራሮች በኢትዮጵያ ስታቲስቲክ አገልግሎት የስራ ጉብኝት አደረጉ። ከፍተኛ አመራሩ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ሶስት ዓመታት የተከናወኑ የሪኢኖቬሽንና ከቴክኖሎጂ አንፃር የተሰሩ ስራዎችን ጎብኝተዋል።
ተቋሙ በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ግንቦት 21/2018 ዓ.ም፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ከ8 መቶ ሺ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ። ተቋሙን ወክለው በጋሞ ዞን ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት የተቋሙ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብነት ሐዋዝ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ መረጃዎችን በማመንጨትና በማሰራጨት ሙያዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ከህዝብ ጎን የሚቆም ተቋም መሆኑን ገልፀው፣ […]
በተቋሙ የስራ አፈፃፀምና ቀጣይ የስራ አቅጣጫዎች ላይ ውይይት ተደረገ

ግንቦት 18/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ሶስት ተከታታይ ዓመታት ባከናወናቸው የስታቲስቲክስ ልማት ፕሮግራም የጥናትና ቆጠራዎች አፈፃፀም ቀርቦ ቀጣይ የስራ አቅጣጫ ላይ ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት መላ ፈፃሚ ጋር ውይይት ተደረገ። መድረኩን በንግግር የከፈቱት የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ዶ/ር ሜሮን ክፈለው ተቋማችን ባለፉት ሶስት ዓመታት ያከናወናቸውን ጥናቶችና ቆጠራዎች በስኬት መጠናቀቅ የሁሉም […]