ሰኔ 25/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የደቡብ ሱዳን ስታቲስቲክስ ቢሮ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኡጉስቲኖ ቲንግ (Augustino Ting /Ph.D.) በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት የስራ ጉብኝት አደረጉ፡፡ ዳይሬክተሩ በተቋሙ የተሰሩ የሪፎርም ተግባራትን የጎበኙ ሲሆን ባደረጉት ጉብኘት ለተቋማቸው የሚሆኑ ልምድና ግንዛቤ እንዳገኙ ገልጾው ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋማቸው ለአፍሪካ እህት ተቋማት ያላቸውን ልምድና እውቀት ለማካፈል ዝግጁ መሆናቸውን አስረድተው፤ዋና ዳይሬክቴሩ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትን መርጠው በመጎበኝታቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልጻዋል።




