ሐምሌ 9/11/2018 ዓ.ም ሀዋሳ
በኢትዮትጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የመካከለኛ ዘመን (2016_ 2018 ዓ.ም) የስታቲስቲክስ ልማት ዕቅዶች አፈፃፀምና በ2019 ዓ.ም የዕቅድ ዝግጅት ላይ በሀዋሳ ከተማ ሲመክሩ የቆዩት የተቋሙ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች በሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት ሀብትን መልሶ ለአገልግሎት በማዋልና ምቹ የስራ ቦታ ለመፍጠር የተሰሩ የሪፎርም ስራዎችን ጎበኙ፡፡
በሀዋሳ ቅ/ጽ/ቤት የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች ለሌሎች ቅ/ጽ/ቤቶች እና በቀጣይ ለሚሰሩት ተመሳሳይ ስራዎች እንደሞዴል የሚወሰዱ መሆኑን ያስረዱት የተቋሙ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅና መላው ሰራተኞች በቅንጅት ለሰሩት ስራና ለተገኘው ውጤት ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡
የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አሰጋሽ አሰፋ በቅ/ጽ/ቤቱ ለተሰሩት ስራዎች ስኬታማነት ለሰጡት ብቁ አመራር በቅ/ጽ/ቤቱ ሰራተኞችና ከ25ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመራሮች ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡




