ነሐሴ 1/2018 ዓ.ም ባቱ
ባለፉት10 ቀናት በባቱ ከተማ በኦሮሚያ ስቴት ዩኒቨርሲቲ ሲሰጥ የቆየው የሲዳማ ክልል የመንግስት ሠራተኞች መረጃ የማረጋገጥ ጥናት የመረጃ ሰብሳቢዎች ስልጠና ተጠናቀቀ።
በስልጠናው መዝጊያ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የተቋሙ ም/ዋ/ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ አይናለም ተሻገር ሰልጣኞች በስልጠና ወቅት እስካሁን በሌሎች የሠራተኞችን መረጃ የማረጋገጥ ጥናት ካከናወኑት ክልሎች የተገኙትን ልምዶችን እንደግብኣት በመውሰድ በክልሉ የሚካሄደውን የመንግስት ሠራተኞች መረጃ የማረጋገጥ ስራ በታቀደው ጊዜና በተሻለ ጥራት ማከናወን እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።



