ነሐሴ 6/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
ለኢትዮትጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤትና ለ26ቱ ቅ/ጽ/ቤቶች ሰራተኞች ዕምርታ በስታቲስቲክስ ልማት በሚል ርዕስ ከነሐሴ4_6/2018 ዓ.ም በተቋማዊ ትራንስፎርሜሽን ላይ አተኩሮ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡
በስልጠናው መዝጊያ መርሀ ግብር ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በስልጠናው ያገኘነውን ዕውቀትና ግንዛቤ እንዲሁም ባለፉት ሶስት አመታት ባከናወናቸው ታላላቅ ተግባራት የተገኙት የአመራር ጥበብ ልምድ ፣ የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ፣ከባለድርሻ አካላት ጋር በትብብርና በቅንጅት መስራትና ሌሎች ምርጥ ተሞክሮዎችን በማስፋትና ስኬቶቻችንን ይበልጥ በማላቅ በስታቲስቲክስ ዘርፍ በአህጉሪቱ መሪ ፤በአለም አቀፍ ስመ-ጥር፣ተወዳዳሪና የልህቀት ማዕከል የሆነ ተቋም ግንባታ እውን ለማድረግ የተጀመረውን ጉዞ ለማሳካት መላው የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በከፍተኛ ሀገራዊ ኃላፊነትና ትጋት መስራት እንደሚጠበቅባቸው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።








