34ተኛ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ባለሙያዎች ማህበር ዓመታዊ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል።

ሐምሌ 11/11/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ባለሙያዎች ማህበር 34 ተኛ ዓመታዊ ጉባኤ ” The role of statistics methods for strengthening digitalization to implement ethiopias development plan” በሚል መሪ ሀሳብ ለሚቀጥሉት ሁለት ቀናት በአዲስ አበባ ይካሄዳል ።

በጉባኤው መክፈቻ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዲጂታላዜሽን ዘርፍ ም/ዋ/ዳይሬክተር ክብርት ዶክተር ሜሮን ክፈለው በሀገራች ብቁ ፣ተወዳዳሪና በስታቲስቲክስ ዘርፍ የልህቀት ማዕከል የሆነ ተቋም ለመገንባት በሚደረገው ጥረት ከሙያ ማህበሩ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ በአጋርነት የሚሰሩ ስራዎችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል ።

ጉባኤው የማኅበሩን ፕሬዚዳንት ዶክተር ታደሰ ካሳሁን ፣ከመላ ሀገራችን ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ፣ከሌሎች የተለያዩ ተቋማትና ከአለምአቀፍ አጋር ድርጅቶች የተወጣጡ የዘርፉ ባለሙያዎች በተገኙበት እየተካሄደ ሲሆን በዘርፉ ላይ የተዘጋጁ የተለያዩ ጥናታዊ ጽሑፎች ቀርበው ውይይት እየተደረገባቸው ይገኛል።

749259045 2456926518153201 2265216529248487498 n
751186363 1609574913931744 4526212040480172453 n
749286066 1018032964311430 2483715242870052471 n