ተቋሙ በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

ግንቦት 21/2018 ዓ.ም፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በጋሞ ዞን በመሬት መንሸራተት ለተጎዱ ወገኖች ከ8 መቶ ሺ ብር በላይ የገንዘብ ድጋፍ አደረገ።

a3a5874
1780076503648

ተቋሙን ወክለው በጋሞ ዞን ተገኝተው ድጋፉን ያስረከቡት የተቋሙ የዋና ዳይሬክተር ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ አብነት ሐዋዝ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ መረጃዎችን በማመንጨትና በማሰራጨት ሙያዊ ኃላፊነቱን ከመወጣት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት ከህዝብ ጎን የሚቆም ተቋም መሆኑን ገልፀው፣ በጋሞ ዞን በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ የተጎዱ ወገኖቻችንን መልሶ ለማቋቋምና ለመደገፍ ከዋናው መ/ቤትና ከ26 ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የሚገኙ አመራሮችና ሰራተኞችን በማስተባበር ከ8 መቶ ሺ ብር በላይ የሰበሰበ ሲሆን በዛሬው ዕለትም ይህንን ለማስረከብ በቦታው መገኘታቸውን ገልፀዋል።

a3a5924

ድጋፉን የተረከቡት የጋሞ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ልዩ አማካሪ አቶ ተስፋፅዮን ዘነበ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በዞናቸው ለደረሰው ጉዳት ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

a3a5892
a3a5820
a3a5834
a3a5919