ሰኔ 23/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የልማት ዕቅድን፣ የፖሊሲ ቀረፃንና ብሔራዊ ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራሞችን የመረጃ ፍላጎትን ለማሟላት እንዲያስችል የተዘጋጀው አዲሱ የስታቲስቲክስ አዋጅ ዛሬ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ፀድቋል፡፡
የፀደቀው የአዲሱ የስታቲስቲክስ አዋጅ በብሔራዊ የስታቲስቲክስ ስርዓት የባለድርሻ አካላትን ሚና እና ኃላፊነት የሚደነግግ፣ ሞያዊ ነፃነትን የሚያረጋግጥ፣ ተቋማዊ አቅምን የሚያጠናክር እንዲሁም ተስማሚ የሆኑ ደረጃዎች፣ ምደባዎችን፣ ሜታ ዳታዎችን እና የስታቲስቲክስ ስርዓቶችን በመጠቀም የሥራና የመረጃ ድግግሞሽ የሚያስቀር በአጠቃላይ በሀገር ደረጃ ወጥ የሆነ የስታቲስቲክስ መረጃ አቅርቦት እና የሕግ ማዕቀፍ እንዲኖር የሚያስችል አዋጅ ነው፡፡
በአዋጁ የተካተቱት ሀገራዊ ግቦች እንዲሳኩ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የበኩላቸውን መወጣት ይጠበቅባቸዋል፡፡




