ሰኔ 19/2018 ዓ.ም ድሬድዋ ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከሐረሪ ክልል ፕላን ኮሚሽን ጋር በመተባበር ከክልሉ የተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለተውጣጡ ባለሙያዎች በስታቲስቲክስ መረጃ አያያዝና ጥራት ላይ በድሬድዋ ከተማ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
በስልጠናው መክፈቻ ላይ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስታቲስቲክስ ሜቶዶሎጂና ሲስተም ልማት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ ተቋማቸው ክልሎች የሚያመነጩትን መረጃ አያያዝና ጥራት ለማሻሻል በከፍተኛ ትኩረት እየሰራ እንደሚገኝ አንስተው፤ በስልጠናው ላይ የተሳተፉ የክልሉ የሴክተር መስሪያ ቤት ባለሙያዎች ስልጠናውን በአግባቡ ተከታትለው ያገኙትን እውቀት ወደ ስራ ሲመለሱ ተግባራዊ ማድረግ እንዳለባቸው መልክታቸው አስተላልፈዋል፡፡
ስልጠናው በስታቲስቲክስ መረጃ አያያዝና ጥራት ላይ በማተኮር ለሚቀጥሉት ሶስት ቀናት በተቋሙ ከፍተኛ ባለሙያዎች ይሰጣል ።









