ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር አካላት ጋር ውይይት ተደረገ

አዲስ አበባ ሐምሌ 4/2018 ዓ.ም

ከአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ከሁሉም ክ/ከተማ ከተወጣጡ ስራ አስፈጻሚዎችና የፕላን ጽ/ቤት ሀላፊዎች ጋር በከተማው እያተከናወነ የሚገኘው የቆጠራ ካርታ አብዴቲንግ የመስክ ስራ ሪፖርት ላይ በአዳማ ከተማ ውይይት ተደረገ።

በውይይቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው በከተማው እየተከናወነ የሚገኘው የቆጠራ ካርታ ወቅታዊ የማድረግ ስራ በከተማው ለሚከናወኑ የስታቲስቲክስ ስራዎች የመረጃ ጥራትና ወቅታዊነት አስፈላጊ መሆኑን በማስረዳት የቆጠራ ካርታ ወቅታዊ የማድረግ ስራው በታቀደዉ ጊዜ እንዲጠናቀቅ ለስራው ለተመደቡት የመስክ ሰራተኞች ፣የማረፊያ ቦታ ማመቻቸትና መንገድ የሚመሩ አካባቢውን የሚያውቁ ሰዎችን በመመደብ የመስተዳድሩ አመራሮች ለስራው ትኩረት እንዲሰጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የጂኦስፓሻል ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ወንደሰን ነገሳ የባለፈው አምስት ወራት ስራው ፤አፈጻጸም ሪፖርት አቅርበው ውይይት የተደረገበት ሲሆን ፣በመጨረሻም ሁሉም ክ/ከተማዎች ለስራው ትኩራት ለመስጠት የጋራ መግባባት ላይ ተደርሶ ውይይቱ ተጠናቋል።

t8a3961
t8a4003
t8a3960