9ኛው የተባበሩት መንግስታት ቢዝነስና የንግድ ስታቲስቲክስ የባለሙያዎች ስብሰባ ተጠናቀቀ

ሰኔ 18/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

ላለፋት ሶስት ቀናት በአዲስ አበባ የአፍሪካ ህብረት ሲካሄድ የቆየው 9ኛው የተባበሩት መንግስታት ቢዝነስና የንግድ ስታቲስቲክስ ባለሙያዎች ስብሰባ ተጠናቋል፡፡

በመድረኩ መክፈቻ ላይ ተገኘተው መልዕክታቸውን ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋማቸው ወቅታዊ እና ጥራቱን የጠበቀ የቢዝነስና የንግድ ስታቲስቲክስ ለፖሊሲ አውጪዎች እያቀረበ እንደሚገኘ አስረድተው በዚህ ስብሰባም ከዘርፉ ባለሙያዎች የሚቀርቡትን የተሻሉ ሜቴዶሎጂዎችና ንድፈ ሀሳቦችን እንደግብዓት በመውሰድ የመረጃውን ጥራት በቀጣይነት ለማሻሻል እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡

በመድረኩ የቢዝነስና የንግድ ስታቲስቲክስ ለማዘመን የሚያግዙ ሜቴዶሎጂ፣ ንድፈ ሀሳቦች እንዲሁም ስታንደርድና የጥራት ማዕቀፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ስብሰባውን የአፍሪካ ስታቲስቲክስ (STATAFRIC) እና በተባበሩት መንግስታት ስታቲስቲክስ ዲቪዥን በጋራ ያዘጋጁት ሲሆን በመድረኩ ከአፍሪካና ከአለም ሀገራት የተወጣጡ በዘርፋ ከፍተኛ ልምድና ዕውቀት ያላቸው ባለሙያዎች ተሳትፈውበታል።

photo 2026 06 26 12 46 54
photo 2026 06 26 13 09 45
photo 2026 06 26 13 10 32
photo 2026 06 26 12 46 49
photo 2026 06 26 13 09 55