ለተቋሙ ሴቶች የአቅም ግንባታ ስልጠና ተሰጠ

aa3a1441

ግንቦት 25/2017ዓ.ም አዳማ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሴቶችን ለማብቃት የሚያስችል የአቅም ግንባታ ስልጠና ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትና ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተውጣጡ ባለሙያዎች ሰጠ።

aa3a1463
aa3a1437

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብነት ሀዋዝ እንደተቋም ሴቶችን ማብቃትና ወደ አመራር  ማምጣት ላይ ትኩረት ተደርጎ እየተሰራበት መሆኑን አንስተው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በሰራው ሪፎርም ሴቶችን ወደ አመራር በማምጣት ሌሎች ባለሙያዎችንም ለማብቃት እየሰራ እንደሆነ ገልፀዋል። 

ስልጠናውን በስርዓተ ፆታ፣ የማካተት ፅንሰ ሀሳብ አስፈላጊነት፣ ስልቶች፣ ተግዳሮቶችና ልዩ ትኩረት የሚፈልጉ የማህበረሰብ ክፍሎች  ፍላጎቶች ላይ ከሴቶችና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በመጡት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ጌታቸው ካሴ እየተሰጠ ይገኛል።

aa3a1482

ስልጠናው ከተለያዩ የስራ ክፍል ለተውጣጡ 45 ባለሙያዎች ለቀጣይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀግብር ለመረዳት ተችሏል።