
ሐምሌ 16/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በመካከለኛ ዘመን (ከ2016-2018ዓ.ም) በስታቲስቲክስ ልማት ዕቅድ ለማሳካት ከታቀዱት አራት ትላልቅ ተግባራት ሶስቱን ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ገለፀ።

በ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀምና 2018 ዓ.ም ዕቅድ ላይ ለመወያየት የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በተገኙበት መድረክ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት (ከ2016-2018ዓ.ም) ለማሳካት ካቀዳቸው ተግባራት መካከል የኢትዮጵያ ስነ-ህዝብና ጤና ጥናት የመስክ ስራ ሙሉ በሙሉ በማጠናቀቅ፣ የግብርና ቆጠራና ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት የመስክ ስራው ከ90% በላይ በማድረስ ውጤታማ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባቀረበው የ2017 ዓ.ም ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ላይ ተገለፀ።
በአዲሱ በጀት ዓመትም በሀገራችን ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራን ለማካሄድ የሚያስችል የቅድመ ዝግጅት ተግባራት መጀመሩን ታውቋል።
