ህዳር 27/2017 ዓ.ም፤ በደቡብ ክልል የመስክ ሥራ ጉብኝት እያደረገ የሚገኘው የተቋሙ ከፍተኛ አመራር ቡድን በክልሉ በተመረጡ የቆጠራ ቦታዎች እየተካሄዱ የሚገኙት ጥናቶችና ቆጠራ የመስክ ሥራዎች በየደረጃው በሚገኙት የክልሉ አመራሮች ትኩረትና ድጋፍ በሚያገኙበት ሁኔታ ላይ ከክልሉ ፕሬዝዳንት ክቡር አቶ ጥላሁን ከበደ ጋር ውይይት አደረጉ። ተቋሙ በክልሉ እያካሄደ የሚገኝው ጥናቶችና ቆጠራ የመስክ ሥራዎች አሁን ያሉበት ደረጃና በቀጣይ የክልሉ አመራር ትኩረትና ድጋፍ ስለሚፈልጉ ጉዳዮች በሚመለከት በተቋሙ የስነ-ህዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይናለም ተሻገር ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ክቡር ፕሬዝዳንቱ ተቋሙ እያካሄዳቸው ከሚገኘው ጥናቶችና ቆጠራ የሚገኙ መረጃዎች ለክልላቸውም ሆነ ለሀገር ልማት የጎላ ፋይዳ ያላቸው መሆናቸው በማስረዳት በክልላቸው በየደረጃው የሚገኘው አመራር በተቋሙ በቀጣይ ትኩረትና ድጋፍ የሚጠይቁ ጉዳዮች ላይ አስፈላጊውን ትኩረት ሰጥተው እንደሚደግፉ፣ አመራር እንደሚሰጡና እንደሚከታተሉ ገልፀዋል።
