ሰኔ 17/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተቋማዊ የመረጃ ጥራት ቁጥጥር አቅምን ለማሳደግ የሚያስችል ስልጠና ከተቋሙ የተለየዩ ስራ ክፍሎች ለተወጣጡት ከፍተኛ ባለሙያዎች ከስታቲስቲክ ኖርዌይ በመጡ በዘርፋ የተሻለ ልምድና ዕውቀት ባካበቱ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።

ስልጠናው ተቋሙ በስታቲስቲክስ መረጃ ጥራትና አቅርቦት ተወዳዳሪና በሂደትም የዘርፋ የልህቀት ማዕከል ለመሆን የጀመረውን ጉዞ እውን ለማድረግ የሚያስፈልገውን የሰው ሀይል ለመፍጠር የጎላ ፋይዳ ያለው ሲሆን ስታቲስቲክ ኖርዌይ የተቋሙን የመረጃ ጥራት ቁጥጥር አቅም ግንባታና ሌሎች የሪፎርም ተግባራት እንዲሳኩ እገዛ እያደረጉ ከሚገኙ አለም አቀፍ ባላድርሻ አካላት መካከል አንዱ ነው።

