ሐምሌ 5/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዋና መስሪያ ቤትና የ26ቱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ኃላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ የሚገኛው የ2017 ዓ.ም የተቋሙ ስራ አፈፃፀም ግምገማ መድረክ ሁለተኛ ቀን ውሎ በ2018ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጀ ለመጀመሪያ የሚካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ መሪ ዕቅድ ገለፃ በቢዝነስ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በግምገማ መድረኩ ማጠቃለያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በ2017 ዓ.ም ስራ አፈፃፀም የተገኙትን ጠንካራ ተሞክሮዎችን አጠናክሮ በመቀጠልና የታዩትን ክፍተቶች በመፍታት በ2018ዓ.ም የተቋሙ ስራ ዕቅድ የሚከናዋኑ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ፣ የስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት፣ ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናትና የግብርና ቆጠራ ውጤት ሪፖርት ዝግጅት ተግባራትን በተሟላ መልኩ ለመሳካት በየደረጃው የሚገኘው የተቋሙ አመራርና መላው ሠራተኞች በቂ ዝግጅት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ቀጣይ የስራ አቅጣጫ በመስጠት የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል።



