የ2017ዓ.ም አረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ተካሄደ

1t8a4119.jpg
1t8a4131.jpg

ሐምሌ 17/2017ዓ.ም አዳማ፣
የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች “በመትከል ማንሰራራት” በሚል መሪ ቃል የ2017 ዓ.ም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር በምስራቅ ሸዋ ሎሜ ወረዳ የችግኝ ተከላ አካሄዱ።

1t8a4080.jpg


መርሀግብሩን ያስጀመሩት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ጥሩማር አባተ በባለፉት ሰባት ዓመታት በክቡር ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶ/ር አብይ አህመድ አመራር ሰጪነት የተጀመረውን የአረንጓዴ አሻራ የማኖር ዘመቻ ስራ ሳይቆራረጥ በመላ ሀገራችን በተመረጡ ቦታዎች የተካሄደ ሲሆን የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብሩ የአየር ንብረት ለውጥ ተፅዕኖንና የአፈር መሸርሸርን በመከላከል፣ የምግብ ዋስትናን ከማረጋገጥ አንፃር ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገቡን በማንሳት በ2017 የምናካሂደው የአረንጓዴ አሻራ የዚሁ ውጤታማ ተግባር ቀጣይ መሆኑን በማስረዳት በየዓመቱ በዚህ ስራ በመሳተፍ አሻራቸውን ላኖሩ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማት አመራሮችና ሰራተኞች ምስጋናቸውን አቅርበው መርሀ ግብሩን አስጀምረዋል።

1t8a4146.jpg
1t8a4185.jpg


በችግኝ ተከላ መርሀ ግብሩ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት የተውጣጡ 500 ሰራተኞች10,000 ችግኞች የተከሉ ሲሆን በመርሀ ግብሩ በመሳተፋቸው ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይም የተከሉትን ችግኝ እንደሚንከባከቡ አስረድተዋል።

1t8a4196.jpg
1t8a4384.jpg
1t8a4308.jpg