
ህዳር 29/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከጥቅምት 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ በመስክ ሲካሄድ የቆየው የመጀመሪያ ዙር የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የምዝገባ ስራ አፈፃፀም ሪፖርት ቀርቦ ተገመገመ።

በኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራው የመጀመሪያ ዙር የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የምዝገባ ስራ አፈፃፀም ሪፖርት 26ቱን ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ስር የሚገኙትን የቆጠራ ቦታዎችንና አንድ ልዩ የቆጠራ ቦታ ሲያተባብሩ በቆዩት አስተባበሪዎች በመስክ ስራው የነበረው አጠቃላይ የድርጅቶች የምዝገባ ሽፋን፣በመረጃ መሰብሰብ ወቅት ያጋጠሙ ችግሮችና የተወሰዱ መፍሔዎች ላይ ያተኮረ ሪፖርት ቀርቦ የተገመገመ ሲሆን የመጀመሪያ ዙር የቆጠራው የመስክ ስራ አፈፃፀም በዕቅዱ መሠረት በጥሩ ሁኔታ የተከናወነ መሆኑ ተገምግሟል።



የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመጀሪመያ ዙር የመስክ ስራ አፈፃፀም ውጤታማ ከመሆኑም በተጨማሪ በቀጣይ የቆጠራው ወሳኝ ምዕራፍ የሚከናወኑ ተግባራትን ለማሳከት ምን ላይ ትኩረት አድርገን መስራት እንዳለብን የሚያግዙ ግብዓት ያስገኘ ሪፖርት መሆኑን አንስተው የመጀመሪያ ዙር የቆጠራውን የመስክ ተግባራት ለማሳከት ተግባራዊ ካደረግነው የተናበበና አሳታፊ ስትራቴጅክ አመራር የተገኙትን መልካም ተሞክሮዎችን ይበልጥ በማጠናከርና በማሳደግ እንዲሁም የተለዩትን ክፍተቶች በማስተካከል ቀጣይ የቆጠራው ወሳኝ ተግባራትን በስኬት ለመወጣት የሚያስችል ፈጠራና ፍጥነት የታከለበት አስቻይ የአደረጃጀት፣ የሰው ሀይል ስምሪት፣የመረጃ ጥራት ቁጥጥር ዘዴ መተግበር የሚያስችል የስራ ላይ ዝግጅት በሁሉም ደረጃ መደረግ እንዳለበት የስራ መመሪያ የሰጡ ሲሆን በቆጠራው የመጀመርያ ዙር የመስክ ስራ አፈፃፀም ለተገኝው ውጤት የተቋሙ አመራርና መላው ሰራተኞች፣ በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት የአስተደዳር አካላት፣መረጃ ሰጪ የህብረተሰብ ክፍል ላሳዩት ትጋትና ትብብር ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይ የሚከናወኑ የቆጠራው ተግባራትን ለማሳካት በመጀመሪያ ዙር የታየው ትጋትና ትብብር ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


