
መጋቢት 4/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሴቶች ቀንን “50 ዓመት የሴቶች ድምፅ ለእኩልነትና ለበለፀገች ኢትዮጵያ” በሚል መሪ ቃል በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ተከበረ።

በበዓሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስነ-ህዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ዓይናለም ተሻገር የሴቶች ቀን ስናከብር ከመብት ጥያቄ ባለፈ የእውቀት ነፃነት፣ ለተቋም ለውጥ ትልቅ ተምሳሌት ነው ያሉ ሲሆን እንደተቋምም ሴቶችን ወደአመራር ከማምጣት አንፃርና የመካከለኛ ዘመን እቅድ ስራዎችን በስኬት እያጠናቀቅንበት ያለንበት ወቅት መሆኑ ልዩ ያደርገዋል ሲሉ ገልፀዋል።

የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ አዚዛ እስማኤል በዓሉን ማክበር ያስፈለገበት ዋና ዓላማ ሴቶች በሀገሪቱ በሚካሄደው ዘርፈ ብዙ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የሚኖራቸው የላቀ ተሳትፎ እና ተጠቃሚነት እንዲሁም በተለይ የኢኮኖሚ ውስንነት፣ ፆታን መሰረት ያደረገ ጥቃትን ለማስቆም ነው ሲሉ ገልፀዋል።

በዕለቱ በዓሉን በማስመልከት የተዘጋጀ አጭር ተውኔትና የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄዷል።



