ለተቋሙ ባለሙያዎች በሜታ ዳታ ላይ ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ

ነሐሴ 22/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከኖርዌይ ስታቲስቲክስ ጋር በመተባበር ከተቋሙ የተለያዩ ስራ ክፍል ለተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች በሜታ ዳታ አስፈላጊነትና አዘገጃጀት ላይ በተቋሙ የስልጠና ማዕከል ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ፡፡

የስልጠናው መጠናቀቂያ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኙትን ዕውቀትና ግንዛቤ ወደ ተግባር እንዲለወጡ የስራ መመሪያ ሰጥተው ፤ለተደረገው ድጋፍ የኖርዌይ ስታቲስቲክስንና ስልጠናውን ሲሰጡ ለቆዩትን የኖርዌይ ስታቲስቲክስ ከፍተኛ ባለሙያ ሚስተር አላን ሔብሪሰንን(Allan Hebrysson) አመስግነዋል።

a3a4497
a3a4563
a3a4520
a3a4526

News