ነሐሴ 30/2018ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክ አገልግሎት ከመስከረም 2017ዓ.ም ጀምሮ ለአንድ ዓመታት ስያካሄድ የቆየው የብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት አካል የሆነውን የሥራ ሥምሪትና የፍልሰት ስታቲስቲክስ ጥናት ውጤት ሪፖርት ይፋ አደረገ፡፡
በመረጃ ስርጭት ወርክሾፕ ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ባለፉት የመካከለኛ ዘመን(2016-2018) በስታቲስቲክስ የልማት እቅድ ከታቀዱት ዋና ዋና የመረጃ ልማት ውስጥ በየወሩ ከሚሰራጨው የገበያ ዋጋ መረጃ በተጨማሪ የስነ ህዝብ እና ጤና ጥናት ተጠናቆ ለተጠቃሚዎች ይፋ መደረጉን አንስተው በዛሬው ዕለት የስራ ስምሪት እና የፍልሰት መረጃዎችን ለተጠቃሚዎች ይፋ እንደሚደረግ ገልጸው፤ ይፋ የሚደረገው ሀገር አቀፍ የሥራ ሥምሪትና ፍልሰት መረጃዎች መንግስታዊ ወቅታዊ የሆነ የሥራ ሥምሪት እና የፍልሰት ፖሊስና ዕቅድ ለማዘጋጀት እንዲሁም ክትትልና ድጋፍ ለማድረግ ቁልፍ ሚና እንደሚኖረው አስረድተው ፣ተቋሙ በዚህ ደረጃ ውጤታማ እንዲሆን መንግስት ለስታቲስቲክስ ልማት በሰጠው ትኩረት ሀብት እና ሎጂስቲክስ እንዲሟላ በማድረግ፣የፕላን እና ልማት ፣የገንዘብ ሚኒስቴር፣የተለያዩ መንግስት ሴክተሮች ፣የክልሎችና የከተሞች መስተዳድር አካላት ፣ የሙያ ማህበራት እና የጥናት ኢንስቲትዩቶች፣ ዩንቨርስቲዎች ፣የሀገራችን ቴክኒክ እና ሙያ ኮሌጆች ፣ የአለም የሥራ ድርጅት(ILO) እና የአለም ስደተኞች ድርጅት(IOM)) ለተደረገው የቴክኒክ ፤ፋይናንስ ድጋፍና ትብብር እንዲሁም ለዚህ ቀን እስከምንደርስ ድረስ ሙያው የሚጠይቀውን ዲሲፕሊን ጠብቀው ፤ሥራውን በላቀ ደረጃ እንዲፈጸም ላደረጉት ከተቋሙ ከፍተኛ አመራር እስከ መረጃ ሰብሳቢዎች ድረስ ሀላፊነታቻውን በአግባቡ ለተወጡ መላው የአገልግሎቱ ባለሙያዎች ምስጋና አቅርበዋል፡፡
መረጃ ስርጭት ወርክሾፕ ላይ ተገኘተው የመክፍቻ ንግግር ያደረጉት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ በረከት ፍስሃጽዮን ኢትዮጵያ የስታቲስቲክስ መረጃ ሉአላዊነቷን ለማረገጋጥ የሚያስችላትን ክ2016_2018 ዓ.ም የቆየ ሶስት ዓመታት የስታቲስቲክስ ልማት ስትራቴጅ ቀርጻ ተግባራዊ ማድረግ እንደተቻለ ገልጽው ዘሬ ይፋ የተደረጉት የሥምሪት እና የፍልሰት መረጃዎች ፤ለቀጣይ አመታት በሀገራችን የሥራ ሥምሪትና ፍልሰትን በሚመለከት ለሚዘገጁት ፖሊስ፤ ስትራቴጅና ዕቅድ ቀረጻ እንደ ዋናኛ ግብዓት እንደሚያገለግል በማስረዳት የጥናቱ መስክ ስራና ሪፖርት ዝግጅት በስኬት ተጠናቀው ለተጠቃሚዎች እንዲደርስ በትጋት ለሰሩት፣ ለተቋሙ ከፍተኛ አመረራሮች ፣ለመላው ሰራተኞች፣ድጋፍና ትብብር ለደረጉ ለፌዴራል፣ ለክልል የመንግስት አካለትና ሌሎች ባለድርሻ አካለት ምስጋና አቅርበዋል፡፡
የአለም አቀፍ የስራ ድርጅት (International lobour Organization/ILO) የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት ዋና ዳይሬክተር አቶ ኩንቡላ ነዳበ ( Mr. Khumbula Ndaba) ድርጅታቸው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክ አገልግሎት ወቅታዊና ጥራቱ የተሞላ የሰው ሀይል ስምሪት መረጃ ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት መደገፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጾዋል።
የመረጃው ተጠቃሚዎች መረጃውን ከዛሬ ጅምሮ ከተቋሙ ድረ-ገፅ www.ess.gov.et. ላይ ገብተው ማግኘት እንደሚችሉ ተገልጿል፡፡









