የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞችን መረጃ የማረጋገጥ የመስክ ስራ ለሚያስተባብሩ ባለሙያዎች የስራ ስምሪት ተሰጠ

a3a2832 2

ሚያዚያ 26/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትና ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ለሚያካሂደው የመንግስት ሰራተኞች መረጃ የማረጋገጥ የመስክ ስራ ለሚያስተባብሩ ከዋናው መ/ቤት ወደ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለሚሄዱ ባለሙያዎች የስራ ስምሪት ተሰጠ።

a3a2844 2

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የስነ ሕዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ አይናለም ተሻገር የመንግስት ሰራተኞች መረጃ ለማረጋገጥ ስራ የሚያስፈልገውን ስልጠና ተጠናቆ የሰለጠነው የሰው ሀይል ከዛሬ ጀምሮ ወደስራ መግባቱን አንስተው፤ ከዋናው መስሪያ ቤት ይህን ስራ ለመደገፍ የሚሄዱት ባለሙያዎች ስራው በመስክ ላይ በታቀደው መልኩ እየተካሄደ መሆኑንና በፅንሰ ሀሳብና በተግባር የተሰጠው ስልጠና ስራ ላይ መዋሉን በየቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ በመገኘት በመደገፍና በማስተባበር፣ የሚያጋጥሙ ችግሮችን በመፍታት ስራውን ለማሳካት ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ሲሉ የስራ ስምሪትና መመሪያ ሰጥተዋል።

a3a2848 2

ለስራው የመስክ ስራ ድጋፍ የሚሰማራው የሰው ሀይል የቴክኒክ፣ የሎጂስቲክና የICT ቡድን በተመደቡበት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የተሰጣቸውን ስራ በትጋት እንዲያከናውኑ ከዋናው መ/ቤት የስራ መመሪያ ተላልፏል።

a3a2861 2
a3a2870 2
a3a2867 2
a3a2872 2