መጋቢት 19/2017ዓ.ም አዳማ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የተቋሙ ባለሙያዎች ስለህጋዊ አሰራር ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ የሚያግዝ ስልጠና ከ26ቱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተውጣጡ ባለሙያዎች በአዳማ ከተማ እየተሰጠ ይገኛል።
ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የስታቲስቲክስ ሲስተም ልማት እና ሜቶዶሎጂ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ እንዳሉት ተቋሙ በተያዘው አመት ትላልቅ ጥናቶችና የቆጠራ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑን ገልፀው ለነዚህ ስራዎች የተሰማራውን የሰው ሀይልና ለስራው የሚያገለግሉ ቁሳቁሶች በህግ አግባብ ስራ ላይ መዋላቸውንና በቀጣይ የሚከናወኑ ስራዎች ህግን መሰረት ያደረጉ ብቻ እንዲሆኑ ሰልጣኞች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።
ስልጠናው በተቋሙ በተለያዩ ስራ ክፍል የሚያገለግሉ ባለሙያዎች የዕለት ተዕለት ስራቸውን እንዴት አድርገው በህጋዊ አሰራር በቻ መፈፀም እንዲችሉ በሚያግዛቸው ጉዳዮች ላይ አተኩሮ ለሰባት ቀናት ከፍትህ ሚኒስቴር በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል።




