የመንግሥት ሠራተኞች መረጃ የማረጋገጥ ስራ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ ተካሄደ

ሐምሌ 17 ቀን 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ

የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን፡ የመንግሥት ሠራተኞች የፐርሶኔል መረጃ የማረጋገጥ ስራ አፈፃፀም ላይ ያተኮረ የምክክር መድረክ አካሄደ።

የኮሚሽኑ ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ሀይሌ በመክፈቻ ወቅት ባደረጉት ንግግር፣ ግልጽ፣ ቀልጣፋና በቴክኖሎጂ የተደገፈ ዘመናዊ የሲቪል ሰርቪስ ሥርዓት ለመገንባት የመረጃ ጥራትን ማረጋገጥና ዲጂታላይዜሽንን ማፋጠን ወሳኝ መሆኑን አንስተው፤ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እየተከናወነ የሚገኘው የመንግሥት ሠራተኞችን መረጃ የማረጋገጥ ስራ እንዲሳካ ተቋማት ትኩረት እንዲሰጡ ጥሪ አቅርበዋል።

የመንግሥት ሠራተኞች መረጃ የማረጋገጥ ስራ የእስካሁኑ አፈፃፀም በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የማህበራዊና አካቶ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ ጥሩዘር ተናኜ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የመረጃ የማረጋገጥ ሥራን በተያዘው የጊዜ ገደብ ለማጠናቀቅ፣የጋራ መግባባት ላይ በመድረስ የምክክር መድረኩ ተጠናቋል።

በመድረኩ ከ400 በላይ ከተለያዩ የመንግሥት ተቋማት የተወከሉ ሚኒስቴር ድኤታዎች፣ የተለያዩ ሥራ ክፍሎች ኃላፊዎች፣ባለሙያዎችና ባለድርሻ አካላት ተሳትፈዋል።

753247622 1012701694705612 1959594634205035210 n
753546304 1044139074780978 6604571495600811935 n
754497248 1010393638469978 7044729015475813274 n