ህዳር 6/2018 ዓ.ም
ከጥቅምት 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተካሄደ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመስክ ስራ ስምሪት ለመደገፍ ከዋና መስሪያ ቤት ወደ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተሰማርቶ የነበረው የሎጅስቲክስ ተግባራት ድጋፍ ሰጪ ቡድን የሃያ ቀናት ቆይታ የስራ አፈፃፀም ተገመገመ።


ድጋፍ ሰጪ ቡድኑ በየቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በነበራቸው ቆይታ ለቆጠራው የመስክ ስራ አስፈላጊ የሆኑትን የፋይናንስ፣ የሰው ሀይል፣ የታብሌትና ተያያዥ ግብዓቶች እና የትራንስፖርት አቅርቦት እንዲሟላ ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ባለሙያዎች ጋር በመቀናጀት ያከናወኑት ተግባራት ውጤታማ መሆኑን ከቀረቡት የስራ አፈጻጸም ሪፖርታቸው ለመረዳት ተችሏል።

የግምገማ መድረኩን የመሩት የተቋሙ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤቢሳ አሰፋ የቡድኑ አባለት የተሰጣቸውን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት ላደረጉት ጥረትና ለተገኘው ውጤት ተቋሙ በመወከል ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም የቆጠራው ስራ እስከሚጠናቀቅ ድጋፍ የሚያስፈልገቸው ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች በመለየት ድጋፉ የሚቀጥል መሆኑን አውቀው ሁሌም ዝግጁ መሆን እንዳለባቸው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።
