የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት አጠቃቀም ላይ ስልጠና ተሰጠ

ሰኔ 16/2017ዓ.ም፣ ሶዶ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት (Integrated management system (IMIS)) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ 25 ሴክተሮች መስሪያ ቤቶች ለተወጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

photo 2025 06 23 19 01 03 2

ተቋሙ ከተለያየ ምንጭ የሚሰበስባቸውን የስታቲስክስ መረጃዎችን በሳይንሳዊ ዘዴ በመተንተን ሪፖርቶቹን ተደራሽ ለማድረግ ጥቅም ላይ ካዋላቸው ዲጂታል የመረጃ ስርጭት መሳሪያዎች መካከል አንዱ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት (Integrated management system (IMIS) ሲሆን የስርዓቱ አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል። 

photo 2025 06 23 19 01 04 2

በዚሁ መነሻ ተቋሙ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮና ከክልሉ 25 ሴክተሮች ለተወጣጡ 100 ባለሙያዎች ስልጠና የሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ወደ ስራ ቦታቸው ሲመለሱ ያገኙትን ልምድና ዕውቀት የመረጃ አጠቃቀም ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ በክልሉ ለእቅድና ክትትል የስታቲስቲክስ መረጃን የመጠቀም ፍላጎትና ግንዛቤ በማሳደግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።

photo 2025 06 23 19 01 03 3
photo 2025 06 23 19 01 04
photo 2025 06 23 19 01 05
photo 2025 06 23 19 01 04 3