ሐምሌ 8/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2018ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ለሚካሄደው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የቅድመ ዝግጅት ስራ መጀመሩን በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት በተጋጀው የማስጀመሪያ ፕሮግራም ይፋ አደረገ።

በቅድመ ዝግጅት ተግባራት የቆጠራው ስነ ዘዴ፣ የሰው ሀይል ዝግጅት፣ ለመስክ ስራ የሚውሉ ግብዓቶችና የቴክኖሎጂ ዝግጅት በዋናነት እንደሚከናወኑ የተገለፀ ሲሆን ይህን ስራ የሚያስተባብር ኮሚቴ ከዛሬ ጀምሮ እነዚህን ስራዎች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን በታቀደው ጊዜ ለማጠናቀቅ ወደ ስራ መግባቱን የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ገልፀዋል።

ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ይህ ስራ ከመስከረም ወር ጀምሮ በመላ ሀገራችን ባሉ ከትናንሽ እስከ ትላልቅ የምርትና የንግድ ድርጅቶች ቆጠራ እንደሚካሄድ በመረዳት በየደረጃው ያለው የመንግስት አደረጃጀት፣ በዚህ ቆጠራ መረጃ ሰጪ የሆኑ የኢኮኖሚ ድርጅት ባለቤቶችና መላው የሀገራችን ህብረተሰብ ለስራው ስኬት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።
