
ግንቦት 25/2017ዓ.ም አዳማ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለተቋሙ የካርቶግራፊና ጂ አይ ኤስ ባለሙያዎች በካርታ ማካለል፣ GIS እና Advance Remote Sensing ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ሲሰጠ የቆየው የተግባር ስልጠና ተጠናቀቀ።

በመድረኩ ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጂነር አብዱራዛቅ ዑመር የስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩትና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለሀገራችን ልማት ዕቅድና ክትትል ግብዓት የሚሆኑ የስታቲስቲክስና ጂኦ ስፓሻል መረጃዎች የማቅረብ ሀላፊነት የተሰጣቸው ተቋማት በመሆናቸው በሁለቱም ተቋማት ያለውን ዕውቀትና ልምድ በተለየዩ አግባቦች ተደራሽ ለማድረግ የሚያስችል ስምምነት ተፈራርመው በጋራ በመስራት ላይ እንዲሚገኙ አንስተው ለ15 ቀናት ሲሰጥ ቆይቶ ዛሬ የተጠናቀቀው ስልጠናም የቆጠራ ካርታ ማካለል ስራን በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የGIS እና Advance Remote Sensing ቴክኖሎጂ አጠቃቀም ላይ ያለውን ዕውቀትና ልምድ በተግባር ለማካፈል የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀው፤ ወደተቋማችሁ ስትመለሱ ያገኛችሁትን ስልጠና ተግባራዊ ለማድረግ በትጋት መስራት ይኖርባችኋል ሲሉ በስልጠናው ለተሳተፋት ባለሙያዎች መልዕክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው በተቋሙ የቆጠራ ካርታ ማካለል ስራ በቴክኖሎጂ የተደገፈ ለማድረግ የሚታዩ ክፍተቶችን በመለየት ስራውን በቴክኖሎጂ የታገዘ ለማድረግ የባለሙያዎችን ቴክኖሎጂ የመጠቀም አቅም ለማሻሻል ታስቦ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን ገልፀው በቀጣይም በካርታ ዝግጅት፣ GISቴክኖሎጂና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ተቋሙ ከስፔስ ሳይንስና ጂኦ ስፓሻል ኢንስቲትዩት በጋራ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

የስልጠናው ተሳታፊዎችም ለስራቸው ጠቃሚ የሆነ የጽንሰ ሀሳብና የተግባር እውቀት እንዳገኙ ገልፀዋል።
