
ሰኔ14/2017 ዓ.ም አዳማ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የኦዲት አሰራርን አስመልክቶ በተለያዩ ርዕሶች ላይ ከዋናው መስሪያ ቤት እና ከቅርንጫፍ ለተወጣጡ የስራ ሃላፊዎችና ባለሙያዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ሃላፊ አቶ አብነት ሃዋዝ ባደረጉት ንግግር ስልጠናው በኦዲት አሰራርና መረጃ አያያዝ የሰራተኛውን ክህሎት ለማጎልበት፤ በእውቀት ላይ የተመሰረተ ውሳኔ እንዲሰጡ ባለሙያዎችን ለማብቃት ፤የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ለማሳደግ የተዘጋጀ በመሆኑ ተገቢውን ትኩረት በመስጠት በንቃት በመሳተፍ በስልጠና የምታገኙትን ዕውቅት ተግባር ላይ እንድታውሉ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ስልጠናው ከፌዴራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች ለቀጣይ ሁለት ቀናት በተለያዩ ርዕሶች ላይ እንደሚሰጥ ለማወቅ ተችሏል፡፡

