ሐምሌ 4/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017በጀት ዓመት ያካሄዳቸው የጥናቶችና የቆጠራ ስራዎች አፈፃፀም ሪፖርት የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ፣የዋናው መስሪያ ቤት እና የቅርንጫፍጽህፈት ቤት የስራ ሀላፊዎች በተገኙበት ተገመገመ።

መድረኩን ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋማችን በ2017 በጀት ዓመት ያከናወናቸውን የግብርና ቆጠራ፣ የስነ-ህዝብና ጤና ጥናትና ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት ሪፖርት ስንገመግም በሂደቱ የተገኙ ጥሩ ልምዶች፣ ያጋጠሙ ችግሮችና በቀጣይ ትኩረት የሚፈልጉ ጉዳዮች በውይይቱ ተነስተው ልንማርባቸው እንደሚገባ አንስተው በስራው እስከአሁን በተገኘው ውጤት በከፍተኛ ትጋትና መነሳሳት ለሰሩ መላው የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች እንዲሁም በዚህ ሂደት ውስጥ እገዛ ላደረጉ ሁሉም ባለደርሻ አካላት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።






በበጀት ዓመቱ ሲከናወኑ የነበሩ የስነሕዝብና ጤና ጥናት፣ ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናትና የግብርና ቆጠራ የደረሱበትን የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ገለፃ ቀርቦ ቀርቦ ሰፊ ውይይት የተደረገበት ሲሆን በነገው ዕለትም የውይይት መድረኩ ይቀጥላል።