የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) ለተቋሙ ድጋፍ አደረገ

1t8a3851
1t8a3820

ጥቅምት 14/02/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለስታቲስቲክስ መረጃን ዝግጅት የሚያግዙ የአይ ቲ (IT) ዕቃዎች ድጋፍ አደረገ።

1t8a3801


በርክክብ መርሐ ግብሩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ወቅታዊና ጥራቱን የጠበቀ የስራ ስምሪትና የፍልሰት መረጃዎችን ከተለያዩ የመረጃ ምንጮች በማሰባሰብና ተንትኖ ጥቅም ላይ ለማዋል እየሰራ መሆኑን ገልፀው ዛሬ በዓለም አቀፍ የስራ ድርጅት የተደረገልን ድጋፍ እየተሰሩ የሚገኙትን ለሪፖርት ዝግጅት ያላቸው አጋዥነት ከፍተኛ መሆኑን አንስተው የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) ላደረገው ድጋፍ ምስጋናቸው በመግለጽ በተቋማቱ መካከል ያለው አጋርነት ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

1t8a3864


በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ተገኝተው የድጋፉ ርክክብ ያደረጉት የዓለም አቀፍ የሥራ ድርጅት (ILO) የኢትዮጵያ፣ የጅቡቲ፣ የሶማሊያ፣ የሱዳን እና የደቡብ ሱዳን ካንትሪ ዳይሬክተር የሆኑት ሚስተር ካምቡላ ናዳባ ከተቋሙ ጋር የሌበርና ፍልሰት ስታቲስቲክስን ወቅታዊና ጥራቱን የጠበቀ የመረጃ አቅርቦትን ለማሳደግ የተጀመረው አጋርነት ገልፀው በተቋሙ እየተሰሩ የሚገኙ የሪኢኖቬሽን ስራዎችን ጎብኝተዋል።


በድጋፍ የተገኙት የአይ ቲ ዕቃዎች በ2017 ከመስክ መረጃ መሰብሰብ ተግባር የተጠናቀቀው ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት የመረጃ ትንተናና ሪፖርት ዝግጅት ስራ እንደሚያግዝ የቤተሰብ በጀትና ሌበር ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፉፋ ቡልቶ ገልፀዋል።

aa3a9995
1t8a3893
aa3a0032
1t8a3930