የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ፐርሶኔል መረጃ የማረጋገጥ ጥናት ቀጣይ ተግባራት ላይ ውይይት ተደረገ

ታህሳስ 13/2018 ዓ.ምአዲስ አበባ፣

1t8a7335 2

የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ፐርሶኔል መረጃ ማረጋገጥ ጥናት ቀጣይ ተግባራት ላይ የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ እና የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ በተገኙበት በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት ውይይት ተደረገ።

1t8a7323 2 1
1t8a7339

እስከአሁን ሲከናዋን የቆየው የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ፐርሶኔል መረጃ የማረጋገጥ የሙከራ ጥናት (pilot Testing) አፈጻጸም ሪፖርት በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የማህበራዊ እና አካቶ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ጥሩዘር ተናኜ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከሙከራ ጥናቱ ሪፖርት የተገኙትን ጠቃሚ ግብዓቶችን በማካተትና ለዋናው ቆጠራ የሚያስፈልጉ ቀሪ የመጠይቅ፣የሰው ሀይልና የሶፍት ዌር ዝግጅት በማጠናቀቅ ከመስክ መረጃ ወደ መሰብሰብ ስራ በአጠረ ጊዜ ለመግባት የተቋማቱ ባለሙያዎች በትጋትና በቅንጅት መስራት እንደሚገባ በሁለቱ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች የስራ መመሪያ ተሰጥቷል።

1t8a7328 2