የጋራ መገልገያ ዕቃዎች የዋጋ ጥናት ላይ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች ሥልጠና  ተሰጠ

የካቲት 11/06 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለሚያካሂደው የጋራ መገልገያ ዕቃዎች የዋጋ ጥናት መረጃ ሰብሳቢዎች  ሥልጠና  ተሰጠ።

t8a9355

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከመንግሥት ግዥ አገልግሎት የቀረበው የጋራ መገልገያ ዕቃዎች ዎጋ መረጃ ፍላጎት ለሟሟላት በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው የጋራ መገልገያ ዕቃዎች የዋጋ ጥናት የመስክ ስራ ላይ ለሚሳተፉ 27 ባለሙያዎች ከየካቲት 09 እስከ 13/2018 ዓ.ም  በመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች፣ በዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ አዘገጃጀት፣ በመረጃ አሰባሰብ ሂደት እና በመረጃ ጥራት ቁጥጥር  ላይ ትኩረት አድርጎ የተሰጠ ስልጠና ነዉ ።

t8a9351
t8a9356