
መጋቢት 2/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት 1447ኛው የረመዳንን ፆም ምክንያት በማድረግ ለተቋሙ የእስልምና እምነት ተከታዮች የአፍጥር ፕሮግራም አዘጋጀ።

በፕሮግራሙ ላይ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የዚህ ዓይነት ፕሮግራሞች ተቋማዊ አንድነት የሚያጠናክሩ መሆናቸውን አንስተው በቀጣይም ተቋሙ የሚያከናውናቸው ተግባራት ስኬታማ እንዲሆኑ በአንድነት፣ በመተሳሰብ እጅ ለእጅ ተያይዘን እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።

በፕሮግራሙ ላይ የተሳተፋ ባለሙያዎችም በአፍጥር ፕሮግራሙ ደስተኛ መሆናቸውን ገልፀዋል።






